በአገራችንም ሆነ በውጭም ባሉት ከትልቅ እስክ ትንሽ ሚዲያ የምንሰማው፣ የምናየው ነገር ግራ አጋቢና ጉድ ያሰኛል በተለይ የአገራችን ባለስልጣናት እየሆኑት ያሉትና ለመሆን የሚጣጣሩት ነገር አጀብ ያስኛል ፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ጉደኛው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለWHO (ለዓለም ጤና ተቋም )ለመወዳደር ሲነሳ ይችን አገር የሚመሯት ሰዎች በንዋይ የሰከረው ህሊናቸው ድንበር ተሻጋሪና አደገኛ መሆኑን ያመላከተበተለይ እኛ በውጩ ዓለም ያለን ኢትዩጵያኖች ልንረዳው የሚገባና በርተተን መታገል ያለብን የግዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።|
ከላይ ርዕሴ ላይ እንደጠቀስኩት ባለሜካፑ ዶክተር ቴዎድሮስ ካፈርኩ አይመልስኝ ብሎ በብዙ ነገሮቹ የጠለሽውን ተፈጥሮአዊ ማንነቱን በሜካፕ ቀባብቶ ብቅ ያለው ፤ለመሆኑ ይህ ሰው ለዚህ ስፍራ ይመጥናል ወይ? ለእዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም በሙያው የጤና ሰው ሆኖ በተለያየ ወቅት የአገራቸውን የውጭ ፖሊሲ በችሎታቸው የምዕራባዊያንን ቀልብ የሳቡ ሞግተው ያሽነፉትን ጥቅሟን አስከብረው ካለፉት ከነአክሊሉ ሃብተወልድና መሰሎቻቸው ጋር በማይመጥን መልኩ የኢትዩጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ በታሪክ ስሙን ለማስጥራት ተሰለፈ ሆኖም ግን ወገኖቻችን በተለይ ደግሞ እህቶቻችን በየአረብ አገራቱ ሲገደሉና ሲታሰሩ ጆሮ ዳባ ልበስ አለ ይባስ ብሎ በ2015 እአ ወንድሞቻችን በሊቢያ በርሃ በአሲየስ ሲታረዱ ኢትዩጵያዊ መሆናቸውን እያጣራሁ ብሎ አረፈው ከዚሁም ጉዳይጋር ተያይዞ ከባድ ወቀሳ የደረሰበት ወያኔ የውጭፖሊሲው ከዱሮ የባሰ መበላሸቱ ሲያውቀውና ንዋይ ሲያጥረው በአንድ ውቅት HIV ለእኛ ጥቅም ነው የመጣው ያለውን ይህን ነውረኛ ሰው ከነበረበት ስልጣን አውርዶ ዛሬ ለWHO እንዲወዳደር ከፍተኛ ገንዝብ ተመድቦለት በወገኖቹ ደም ላይ አሁንም ቀልድ የጀመረው ።
በተለያየ ግዜ በተለያዩ የአገሪቱ ከልል የሚሰሩ ዶክተሮች፣ የላብራቶሪ ሰራተኞችና ከሕክምና ሙያ የተያያዝ ስራ የሚሰሩ ሰዎች ጋር በነበረኝ ቅርበት ሁሌ ሲያማርሩ የሚሰማው ነገር ቢኖር በየግዜው በሚፈጥረው የመድሃኒትና የመሰረታዊ መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ላይ ነው ይህ ማለት እንግዲህ ለበሽታ ማስታገሻ ተብሎ የሚሰጠውንም ይጨምራል እንዲያውም አንዳንዶቹ ዶክተሮች ወደውት ከሰባት ዓመት በላይ ዋጋ የከፈሉለትን ሙያ እያማረሩ ግማሹቹ ተሰደዋል ግማሽዎቹ ያችኑ የሁለት ዓመት ግዴታቸውን ከተወጡ በኋላ ከተማ (በተለይ አዲስ አበባ) ገብተው ያዩትን ሁኔታ እንዳላዩ ሆነው ይኖራሉ ሞትና እንግልት የተፈረደበት የገጠሩ ህዝብ ዕድሜ ለነ ቴዎድሮስ አድሃኖም ፖሊሲ እየማቀቀ ይኖራል፤ እንዲያውም ለዚህ ጉዳይ ማመላከቻ ይሆን ዘንድ በአንድ ወቅት አንድ ላብራቶሪ ውስጥ ከህንድ በመጣው የተጭበረበር ኬሚካል ምክኒያት ብዙ ሰው ለሌላ ህክምና ሄዶ ታይፎይድና ታይፈስ አልብህ ተብሎ መመለስ የዕለት ተለት ዜና ሆኖ ነበር በኋላ ላይ በተደረገ ማጣራት ይሄው ኬሚካል ውሃ እንኳን ሳይቀር ፖዘቲቭ እያለ አስቸግሮ ነበር በዚያም ጥርጣሬ ነበር የኬሚካሉ ፎርጅድነት ታውቆ ክገበያ የወጣው ነገር ግን ከዚሁ ጋር በተያያዝ በታዘዘላቸው መድሃኒት ምክኒያት ለጉበትና ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጡ ሰዎች በሆነ ወቅት የተለመደ የነበረው እንግዲህ ይሄን ሁሉ ጉድ የተሽከመው ሰውየ ነው በዓለም መሳቅያና መሳለቅያ ሊያደርገን ድቤውን እየጎሰመ ያለው።
ወደ እናቶችና ህጻናት ሞት ስንመጣ ደግሞ ጉጀለው የወያኔ መንግስት ከIMF ገንዘብ መጠየቂያ ይሆነው ዘንድ በራሱ ቀመር በሰራው አሃዝ አለምን ያታልላል ነገር ግን ውደ ውስጥ ጠጋ ብለን ስናየው በየክልሉና ገጠር ቀበሌው ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሞቱት ህጻናትና እናቶች ቤት ይቁጠራቸው፤ እንግዲህ አስተውሉ በአገሩ ህጻናት ደም ሌላው ደግሞ ሳይማሩ ባስተማሩትና ክብካቤና ክብር በሚገባቸው እናቶች ላይ ያሾፈው ባለሜካፑ ዶክተር ቴዎድሮስ ማን አለብኝነቱን በአለም መድረክ ለማሳየት የደፈረው፤ ወንድሞቸና እህቶቼ በተለይ እኛ በስደት ያለን ኢትዩጵያኖች በተገኘው አጋጣሚ በመረባረብ ይህን የጉጀሌው ተላላኪ ማስቆም ያለብን።
በዚሁ አጋጣሚ በወያኔ ዘመን የተማረና የተመረቀ ልማታዊ ዶክተር እሱ ጋር ሊታከም የመጣን በሽተኛ የሰጠውን መልስ በግጥም መልክ አንድ ጓደኛ ያስቀመጥውን ጀባ ልበልና ላብቃ
ቀንስ
አንጀቱ ተጣጥፎ
እግሩ ተዝለፍልፎ
ለመራመድ ሰንፎ
ገላው ወዙን አጥቶ
ሁለመናው ከስቶ
ደራርቆ ገርጥቶ
በጓደኛው ታዝሎ ጤና ጣቢያ መጥቶ
ሃኪሙ ጋር ቢደርስ ለጉድ እያሳለው
ዶክተር “ያገር ፍርጃ” ምግብ ቀንስ አለው
ብታስደንቀውም ዓለም ተግልብጣ
ማልቀስ ቢፈልግም ብሶቱን ሊወጣ
እንባ አልቆበታል ኬ’ት አባቱ ይምጣ፟
የሚሆነው ቢያጣ ማልቀስ እያማረው እየሳቀ ወጣ