የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመቀሌና በባህር ዳር ከነማ ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ...

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመቀሌና በባህር ዳር ከነማ ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ

ከ15 ቀን በፊት በመቀሌ ከነማና በባህር ዳር ከነማ መካከል በተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በታየው ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በመቀሌ አዲ ሀቂ ስታዲየም በመካሄድ ላይ የነበረው ጫዋታ 60ኛው ደቂቃ አካባቢ ግጭት ተፈጥሮ ጨዋታው መቋረጡ የሚታወቅ ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዕለቱን ጨዋታ ከመሩት ዳኞች ባገኘሁት ሪፖርት መሰረት ተከታዩን ውሳኔ አሳልፋለሁ ብሏል፡፡

“በተካሄደው ጨዋታ የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸውና ከተጫዋቾች ጋር በመደባደባቸው ቡድኑ የ100 ሺህ ብር ቅጣት ና በ20 ቀን ውስጥ ደጋፊዎቻቸውን ስፖርታዊ ጨዋነት አስተምረው ለፌዴሬሽኑ ሪፖርት እንዲልኩ ተወስኗል፡፡
የባህር ዳር ከነማ እግርኳስ ቡድንን በተመለከተ ተጫዋች ኪዳኔ ተስፋይ በጨዋታው ላይ በደረሰበት ጉዳት የመጀመሪያ እርዳታ እንዲያገኝ በስትሬቸር ከሜዳው በሚወጣበት ጊዜ በቀይ መስቀል ሞያተኞች የተፈጸመበት ጥፋት መሆኑን የጨዋታ አመራሮች አረጋግጠዋል፡፡ ምንም እንኳን ተጫዋቹ ጥፋት ፈጽሟል ብሎ ሪፖርት ቢደረግም ችግሩ ሊከሰት የቻለው በቃሬዛ ያዦች በፈጸሙት ጥፋት መሆኑ ታውቋል፡፡ ስለዚህ ተጫዋቹ ያለምንም ቅጣት እንዲታለፍ ተወስኗል፡፡

በተጫዋች ኩማ ደምሴ ፣በተጫዋች ቴዎድሮስ ሙላት፣በተጫዋች ሚኪያስ ግርማ እና በተጫዋች ተስፋሁን ሸጋው የመቀሌ ከተማ ቡድን ደጋፊዎች ወደ ሜዳው በመግባት በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት ራሳቸውን በመከላከል ውስጥ ሆነው ጥፋት የፈጸሙ ስለሆነ ኮሚቴው ጉዳዩን መርምሮ ያለምንም ቅጣት እንዲታለፉ ወስኗል፡፡

በተጫዋች ዘውዱ መስፍን ና በተጫዋች ተዘራ መንገሻ በቀይ መስቀል እርዳታ ሰራተኞች በመደባደባቸው ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ተግባር በመፈጸማቸው እያንዳንዳቸው 4 ጨዋታዎችን እንዲቀጡና 4 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡
አቶ ጥጋቡ አብተው የባህር ዳር ከነማ እግርኳስ ቡድን መሪ በዕለቱ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ዳኞችን በመሳደባቸውና ካላቸው ሀላፊነት አንጻር ለሌሎች አርአያነት የጎደለው ተግባር በመፈጸማቸው 4 ሺህ ብር እንዲከፍሉና 5 ጨዋታዎችን እንዲታገዱ ተወስኗል፡፡

የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ የቡድኑ ወጌሻ አቶ በቀለ መንግስት የቀይ መስቀል ሰራተኞችን በመደባደባቸውና ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በመፈጸማቸው 5 ጨዋታዎችን እንዲታገዱና 4 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡
በመቀሌና በባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የተቋረጠው ጨዋታ በዝግ ስታድየም በመቀሌ እግር ኳስ ቡድን ሜዳ የቀረው የቀረው 16 ደቂቃ ጨዋታ እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡”

የጠቡ መነሻ ምክንያት ጨዋታውን ይመሩት የነበሩት የመሀል ዳኛ 60ኛው ደቂቃ ላይ ለመቀሌ ከነማ “ፍጹም ቅጣት ምት” መስጠታቸውና ባህር ዳር ከነማ ተገቢ ያልሆነና አድሎዊ ነው ማለታቸው እንደሆነ በወቅቱ መገለጹን እናስታውሳለን።

1 COMMENT

  1. I smoked in college for two years and when I saw my aunt dying from lung cancer, not being able to breath but asking for a cigarette, I imteeiamdly quit cold turkey. Why can’t I do the same with food? This is exciting news…

LEAVE A REPLY