/ETHIOPIA Nege News/:- በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞችና በጎንደር፡ በጎጃምና በኮንሶ አካባቢ ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ ጥያቄዎችን ተከትሎ በወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ትእዛዝ ለሰባት ወራት በተለያዩ እስር ቤቶች የቆዩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የመብት ትሟጋቹ ዳንኤል ሽበሽ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የሽብር ቡድኖችን የሚያነሳሳ ምስሎችን በመያዝ በሚል ክስ የቀረበባቸው ጋዘጠኛ ኤልያስ እና የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል ዳናኤል ሽበሽ ፌስ ቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የለጥፏቸው ምስሎች በማስረጃነት መያዛቸው ተዘግቧል፡፡
የቀረበባቸውን ክስ ዛሬ ያደመጠው በፍርደ ገምድልነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ለሰኞ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ክሱ በዚሁ ከቀጠለና ጋዜጠኛ ኤልያስና የመብት ተሟጋቹ ዳናኤል ሽበሽ ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አስር አመት የሚደርስ እስራት ሊወስንባቸው ይችላል፡፡
ኤልያስ ገብሩ በተለያዩ የማህበርዊ ድረ ግጽ ላይ በአገዛዙ ላይ የሰላ ትችት ከመግለጹም በላይ እስክንድር ነጋንና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ሲወተውት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በፌስ ቡክ ገጹ በሚያስተላልፋቸው አጭር የነጻነት መለክቶች በህወሃት መራሹ አገዛዝ ጥርስ ውስጥ እንደገባ ተመልክቷል፡፡
Ethiopia nege May 31,2017