በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በእጅጉ እየተስፋፋ ነው

በአማራ ክልል የኮሌራ በሽታ በእጅጉ እየተስፋፋ ነው

በኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ህዝብ በወባ በሽታ እንደሚጠቃ ጥናቶች አሳሰቡ

/Ethiopia Nege NEWS/፦ ኢትዮጵያ ህዝብ  በከፍተኛና ቀዝቃዛ ቦታዎች (Highlands)  የሚኖር በመሆኑ ብዙ ለወባ በሽታ ተጋላጭ ያልነበረ ቢሆንም አሁን እየጨመረ በመጣው የሙቀት መጠን ምክንያት ኢትዮጵያ ለወባ በሽታ የመጋለጥ እድሏ ከፍተኛ  መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ተናገሩ።

Environmental  Research Letters  የተባለ ተቋም እንዳለው እ.ኤ.አ 1981 ጀምሮ በኢትዮጵያ በየአመቱ  የሙቀት መጠን መጨመር እየተስተዋለ መሆኑን  በኒው ዮርክ  የሚገኙትን “ የማይንና ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ”  ተመራማሪዎችን ጥናት ጠቅሶ አመልክቷል። በዚህም ከስድስት ሚሊዮን  ህዝብ  በላይ በወባ በሽታ ሊጠቃ  እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።

ጥናቱ እንዳለው የወባ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን የሆነው “ፕላስሞዲየም  ቫይቫክስ”  ከ15C ዲግሪ በላይ በሆነ  የአየር ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች  የመሰራጨት  እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል። በዝቅተኛ የሙቀት መጠን የወባ በሽታ ተህዋስያን  የመስፋፋት እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ም በጥናቱ ተጠቅሷል።

እ.ኤ.አ ከ1981 እስከ 2014 ድረስ ኢትዮጵያ በየአስር ዓመቱ  በአማካይ  0.22C (0.4F) የሙቀት መጠን እንደጨመረ ጥናቱ ያመላክታል።

በዓለም  የጤና ድርጀት መረጃ መሰረት በአለም ላይ በ2015 ብቻ  212 ሚሊየን  ሰዎች  በወባ በሽታ የተጠቁ ሲሆን 429 ሺህ ሰዎች ደግሞ በበሽታው  ህይወታቸውን አጥተዋል። በወባ በሽታ የሚያዙና  ህይወታቸውን  ከሚያጡት መካከል 90 በመቶ አፍሪካዊያን ሲሆኑ እድሜቻውም  ከዓምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በከፍተኛ ደረጃ ተጠቂዎች መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል በምዕ/ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የኮሌራ በሽታ እየተስፋፋና ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው ገልጸዋል። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአማራና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች  በተደጋጋሚ ጊዜያት የኮሌራ ወረሽኝ ቢከሰትም አስቀድሞ የመከላከል ሥራዎች ባለመሰራታቸው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይነገራል። በአማራ ክልል ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ደካማ በመሆኑ ለወረሽኙ መስፋፋት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድና እስካሁንም  ድረስ በወረርሽኙ  ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎች  እንዳሉ ቢታወቅም መንግስት በሽታውን አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት(አተት) በማለት የበሽታውን መከሰት ለመደበቅ በመሞከሩ ምክንያት ያደረሰውን ጉዳት በውል ለይቶ ማወቅ እንዳልተቻለ ይታወቃል።

/Ethiopia Nege June 16, 2016/

LEAVE A REPLY