ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት የፈረደበት ፅኑ የ3 አመት የእስር ጊዜ ሊጨርስ ዛሬ ሰኔ 15/09ዓ.ም 3 ወር ከ15 ቀን ብቻ ይቀረዋል። አኔም እንደለመድኩት ዛሬን ካስገቡኝ ብዬ ዝዋይ እስር ቤት ተገኝቻለሁ። ከገባሁ ተሜንም ጠይቄ ልደቴንም አክብሬ እመለሳለሁ፤ ከላገባሁም እስር ቤቱ ደጃፍ ላይ እንደቆምኩኝ ወንድሜን ባዓይነ ህሊናዬ አይቼ እመለሳለሁ ብይ ዝዋይ ተገኝቻለሁ። አንዳንዴ እንደማያስገቡኝም እያወኩ ዝዋይ እስር ቤት ደጃፍ እገኛለሁ፤ ዓይነ ህሊና ሲቀርብ የበለጠ የሚያሳይ ይመስለኛል።
የሆነው ሆኖ ዛሬ ገብቻለሁ በዓይነ ህሊና ሳይሆን በዓይነ ሥጋ ተሜን ለማግኝት አስገብተውኛል። ተሜን አየሁት ፈግግ አንዳለ ነው ከፊትም ከኋላም ወታደሮች አሉ ተነስቼ ጠበኩት መጣ እንደ መጣ እቅፎ ስላም እያለኝ እሺ “ባለ ልደት እንዴት ነህ” አለኝ መለስኩ አሁንም ስለናታታችን ጤንነት ጠየቀኝ መለስኩ ያመጣሁትን ስንቅ አቀበልኩት። ጤንነቱን ጠየኩት ምንም ለውጥ የለውም አለኝ። አጅበው ካመጡት ወታደሮች በተጨማሪ 4 ወታደሮች ተጨምረው በ6 ወታደሮች ተከበን ነው የምናወራው። ህክምና ስለመከልከሉ ስናወራ አንዱ ባለ ማአረግ ወታደር “ይህን ማውራት አትችሉም” አለ ተሜም “የማወራውን አትመርጥልኝም” አለው ወታደሮቹ ተያዩ ተያየተው አንገታቸውን ነቀነቁ በዛቻ ይሁን ተሜ ያለውን በመቀበል አንገታቸውን መነቅነቃቸውን የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው። ተሜና እኔ የምናወራውን አውርተን ጨርሰን።
ለመሰነባበት ተነሳን ተሜ እንደ ታላቅ ወንድም እንደ አባትም እያየኝ “መልካም ልደት” አለኝ በቃ ምሴን አገኘሁ ደስታዬ ጣራ ነካ ይህን ፈልጌ ነው የመጣሁት የመጣሁበትንም ትልቁን የልደት ቀን ማሳመሪያ ቃል ሰማሁ ። ተሜ ሲሄድ ከኋላው አየሁት በአረንጓዴ በቢጫ በቀይ የተሰራ የባንዲራ ቀበቶ አደርጓል ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ቢሆኑም ባንዴራውንም ተሜንም መከለል አልቻሉም ይልቅስ በክብር ያጀቧቸው ይመስላሉ።
ከእስር ቤቱ መውጣት ስጀምር ስሜ ሲጠራ ሰማሁ ዞርኩኝ ከ 6ቱ ወታደሮች አንዱ ወደኔ እየመጣ ነው። ቆሜ ጠበኩት። እንደደረሰ “ልደት እስር ቤት ውስጥ ማክበር አይቻልም” አለኝ ገና መናገር ስጀምር “ጨርስኩ” ብሉኝ ሄደ። ፈገግ አልኩኝ እንግዲህ የተነገረው ተናግረክ ና ለመስማት እንዳታስብ አንደተባለ ገባኝ።
እስር ቤት ግቢ ውስጥ እንደቆምኩኝ ዙሪያውን ተመለከትኩ አሁንም ተሜ ወደ ሄደበት አቅጣጫ አየሁኝ አሳሪ ነን የሚሉ ባለጠመንጃዎች በቦታው ላይ ቢተራመሱም እኔ ባለ ህሊናውን ለሀገሩ ሲል እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው መንገዴ ያለውን ተመስገንን ብቻ ጉልቶ አየሁት። እንደቆምኩ የታወቀኝ እየሄድክ የሚል የጩኸት ድምፅ ነው። ደምፁ ወደ ሰማሁበት ዞርኩ ሌላ ባለጠብ መንጃ ወታደር አየሁ። “እኔማ እሄዳለሁ ያታሰሩትም ይፈታሉ… እስር ቤቶችም ትምህርት ቤት ይሆናሉ… ሀገራችንም ለሚያስብ ሰው እስር ቤት አይኖራትም… ፍትህና ሰባዓዊነት ይነግሳሉ… በህግ የበለይነት አንገዛለን… ጠብ-መንጃዎቹም ዝቅ ይላሉ… ኢትዮጲያዊነት በውዴታ ከፍ ይላል… ይህን ለራሴ እያልኩኝ ልደቴን ዝዋይ እስር ቤት አክብሬ ወጣሁ።
ሰኔ 15/09 ዓ.ም