/ሙሉቀን ተስፋው/
ከፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሕወሓት አጠቃላይ አገሪቱን በቀጥታ ለመቆጣጠር የሚያስችለውን የፖሊስና የጸጥታ በአገር አቀፍ ስታንዳርድ ለማስተዳደር ፖሊስ በአንድ እዝ ሥር መሆን እንዳለበት የሚያዝ አዋጅ ወጥቶ ረቂቁ ሰኔ 30 እና ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ የስብሰባ አደራሽ ለውይይት የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ተገልጿል፡፡
በሕወሓት የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሠፋና በፌደራል ፖሊስ ግርማይ ከበደ የተቀነባበረው የወልቃይት የዐማራ ብሔርተኝነት ጥያቄን ማዳፈን ከከሸፈባቸው በኋላ በደኢሕዴን ተወካዩ ጄኔራል አሠፋ አብዬ ከትግሬ አመራሮች ጋር በመደራደር ሕገ መንግሥቱን የሚጥስ የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን የሁሉንም ክልሎች ፖሊስ ኮሚሽኖች አፕሬሽን እንዲመራ የአዋጅ ረቂቅ በማዘጋጀት የፍትሕ ሚኒስቴሩ አቶ ጌታቸው እና ጀኔራል አሰፋ አብዮ የ9ኙንም ክልል ፖሊስ ኪሚሽን ጄኔራሎችና የፀጥታ ኃላዎች ለማሳመን የታሰበው ስብሰባ 30/09/09 እና 01/11/2009 ዓ/ም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ ተካሄዶ ነበር፡፡
የስብሰባው መሪዎች አቶ ጌታቸው እና አሰፋ ለተሰብሳቢዎቹ የአገርን ደኅንነት ለማስጠበቅ የፖሊስ ስታንዳደርድ ማስጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና በአንዳንድ ክልሎች ያለውን የግለሰብ መሣሪያ አያያዝ አሰራር ለማበጀት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አዛዥነት መመራት እንዳለበት የወጣ አዋጅ ላይ ውይይት ለማድረግ የተሰበሰቡ መሆኑን ከአስረዱ በኃላ የአዋጁ ረቂቅ ቀረበ፡፡ ከሁሉም ክልሎች የመጡ የፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊዎች በተሰበሰቡበት በዚህ ውይይት ከዐማራና ኦሮሚያ ክልል የመጡ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገልጧል፡፡ በስብሰባው የተነሱ ተቃውሞዎች ተብለው የተገለጡት፤
1/ ፌደራል የክልሎችን ፖሊስ እንዲመራ ከታሰበ በቅድሚያ ሕገ መንግሥቱ መሻሻል ያለበት መሆኑን እና ለሕዝብ ቀርቦ ሕዝበ መወያየት ያለበት መሆኑን፣
2/ ከዚህ በፊትም የተከሰቱት ግጭቶች የፌደራል መንግሥት በክልሎች ላይ የገባው ጣልቃ መንስኤ መሆኑን፣
3/ ፌደራል ክልሎችን ሁሉ እንዲመራ የታሰበበት አግባብ ዓላማው ሌላ አጀንዳ ያለው በመሆኑ እና ከዚህ አዋጅ ጀርባ ያለ ድብቅ ዓላማ ወጥቶ መወያየት የሚገባ መሆኑን
4/ ፌደራል በራሱ ክልሎችን ለመምራት ብቃት የሌለው መሆኑ ከተነሱት ጠንካራ ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡
በዚህ ስብሰባ ላይ በሚሰጡት ምላሾች አወያዮቹ አቶ ጌታቸው አምባየ እና አሰፋ አብየ ከፍተኛ ኃፍረት ከፊታቸው ላይ ይነበብ እንደነበር የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
እኙሁ ምንጮች ስለ አዋጁ ዓላማ እንደተገለጸልን ከሆነ የዐማራን ሕዝብ በፌደራል ፖሊስ በኩል መቆጣጠር፣ ሕዝቡን መሣሪያ ማስፈታት እና የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለማፈን የታለመ ነው፡፡ የዚህ አዋጅ መነሻም በጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ላይ የፈፀሙት ሙከራ የቀመሱትን የጀግና ምላሽ ተሞክሮ በማድረግ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከዐማራ ተወክሎ የሔደው የፖሊስ አዛዥ ‹‹የአውጁ ድብቅ ዓላማ ይገለጽልን፣ የክልልን ስልጣን ለመከለስ ከተፈለገ ሕገ መንግስት ሊሰተካከል ይገባል፣ ከዚህ በኋላ በክልላችን ፌደራል ባይገባ መልክም ነው›› በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ የኦሮሚያው ጸጥታ ኃላፊ ኮሚሽነር ደመላሽ ከዚህ ቀደም ፌደራል በነበረበት ጊዜ በእነ ኮሚሽነር ግርማይ፣ ተክላይ፣ ካህሳይ፣ ዓለምፀሐይ ሲደረስበት የነበረውን ግምገማ መልክ የማጥቃት ዘመቻ በሚመስል መልኩ ‹‹ፌደራል ክልል ለመምራት ብቃቱም አቅሙም የለውም፤ አሁን ምን አጣችሁ፣ እንደፈለጋችሁ እያደረጋችሁ አይደል እንዴ፣ ለዚህ ውይይት እኔን ሳይሆን ጨፌውን መጠየቅ ይኖርባችኋል›› በማለት ተናግሯል፡፡ የደኢሕዴኑና የሕወሓት ተወካዮች የረቂቅ አዋጁ ደግፈው ብዙ ለማሳመን ጥረዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ በፌድራል ፖሊስ ውስጥ ሕዝብ እያስጨረሱ ያሉት እና በዚህ አዋጅም ሥልጣን ተሰጥቷቸው ሕዝብ ለመጨረስ ተዘጋጅተው የሚገኙት የደኅንነት ቢሮ ኃላፈው አቶ ጌታቸው፣ የፌድራል ፖሊስ ም/ ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ፣ ኮሚሽነር ተክላይ፣ ኮሚሽነር ፍጹም፣ እና በምርመራ ኮ/ር ረታና ተክላይ እንደሆኑ ምንጮቻችን በዝርዝር ተናግረዋል፡፡