በቅርቡ የተጣለውን የቀን ገቢ ግምት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል

በቅርቡ የተጣለውን የቀን ገቢ ግምት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል

/Ethiopia Nege News/:- የአምቦ፣ ወሊሶ፣ጊንጪ፣ሙገርና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች የተጣለውን የቀን ገቢ ግምት በመቃወም ለ3 ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው።

 ትናንት የጀመረው ይኸው የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሎ፤ ሱቆች፣ሆቴሎች፣ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንገዶችና ሌሎችም የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ሆነው ውለዋል። በአምቦ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

 በጊንጪ ህዝቡ ግብር አንከፍልም፤ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱ የሚሉና ሌሎችም የለውጥ ጥያቄዎች በማሰማት ላይ መዋላቸው ታውቋል። አድማውን ተከትሎ  ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ ወደ ከተሞቹ  መግባቱም ታውቋል።

የጊንጪ ከተማ አስተዳድር ህቡን ለማስፈራራት ሞክረው ባለመሳካቱ፤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ  የተወሰኑ ነጋዴዎችንና ሽማግሌዎችን ጠርቶ በመሰብሰብ “አምና በ2008 ዓ.ም የከፈላችሁበትን የግብር ደረሰኝ  ይዛችሁ በመምጣት ከነገጀምሮ ክፈሉ” በማለት ህዝቡን ለማግባባት እየመከሩ መሆናቸውን ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ ነጋዴዎች አድማውን በመቀላቀል ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙ የአድማ ጥሪ ወረቀቶች እየተበተኑ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ጊንጪ ከተማ ከአመት በላይ የዘለቀው እና በተለይ የኦሮሚያ የአማራ ክልልንና በኮንሶ የተቀሰቀስው ህዝባዊ አመጽ መነሻ እንደሆነች የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በአማራ ክልልም የተለያዩ ቦታዎች ውጥረት መንገሱ ታውቋል። ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ከዚህ በፊት አነስተኛ ግብር ከፋይ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ወደ ደረጃ “ለ” እና “ሀ” ግብር ከፋይ እንዲሸጋገሩ መደረጉ ከፍተኛ ጭንቀት እንደፈጠረባቸው ያነጋገርናቸው የአነስተኛ ግብር ከፋይ(ደረጃ ሐ) ነጋዴዎች ነግረውናል።

LEAVE A REPLY