አነስተኛ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ያመኑትን ቀረጥ ይክፈሉ ተባለ

አነስተኛ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ያመኑትን ቀረጥ ይክፈሉ ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ሰሞኑን በነጋዴዎች ላይ የተጣለውን የቀረጥ ክፍያ ተመን ተከትሎ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እየተቀጣጠለ የመጣውን ህዝባዊ አመጽ ለመግታት አንዳንድ አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ራሳቸው ያመኑትን የቀን የገቢ ቀረጥ እንዲከፍሉ መወሰኑ ተገለጸ፡፡

በተለይ በጉሊት፡ በልብስ ስፌት፡ በቡና በማፍላትና በመሳሰሉ ጥቃቅን ንግዶች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ራሳቸው ያመኑበትን ቀረጥ መክፈል እንዳለባቸው የተወሰነ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መኖራቸው ብቻ በቂ ነው የሚል በርካታ ወቀሳ መድረሱን የግምሩክ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በተለይ አፍቃሬ መንግስት ለሆነው ሪፖርትር ጋዜጣ ስለጉዳዩ ያብራሩት አቶ ከበደ ጫኔ የቀረጥ ግምቱ በአነስተኛ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ከፍተኛ ቅሬታ በማቅረባቸው ያመኑትን እንዲከፍሉ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

በጊንጪ፡ በአምቦና በኮልፌ አካባቢ የተጀመረው ተቃውሞ መነሻ መንግስት እንደሚለው በጉሊትና በመሳሰሉ ጥቃቅን ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ብቻ የተቃውሙት አስመስሎ ምላሽ መስጠት አግባብ አለመሆኑን የገለጹ ነጋዴዎች በአንዳንድ ቦታዎች ሱቆቻቸው እንደሚታሸግባቸው ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም አሁንም ሱቆቻቸውን በመዝጋትና ስራ በማቆም አድማ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

LEAVE A REPLY