አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያሰፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ

አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያሰፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በ2016 የተከሰተው “ኤሊኖ” ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ጠባይ ለውጥ አስከትሏል።ይህን ተከትሎ በተለይ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ድርቅ በመከሰቱ በርካታ ዜጎች በምግብ እጦት እየተገላቱ ነው። ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከቀየው መፈናቀሉን፤ እንስሳት ለሞት መዳረጋቸውን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ህፃናት ትምህርት ማቆማቸውን እንዲሁም በኢትዮጵያ ሶማሌ በሰኔ ወር ብቻ ከ68 በላይ ህፃናት ለህልፈት መዳረጋቸውን ድበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በቦታው ተገኝተው ያዩትን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሪፖርት ማድረጋቸው የቅርብ ጊዜ ሁነት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(OCHA) ትናንት ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው በሚቀጥሉት አምስት ወራት ብቻ 8.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።በጥር ወር 5.6 ሚሊዮን የነበረው የተረጅዎች ቁጥር በፍጥነት በማደግ ወደ 8.5 ሚሊዮን ማሻቀቡን ጠቅሶ፤ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት (እስከ 2017 መጨረሻ) ብቻ ለምግብና ተመሳሳይ ወጭዎች የሚውል 487.7 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ኦቻ በሪፖርቱ ጠቅሷል። 3.6 ሚሊዮን የሚሆኑት ህፃናት፣ እርጉዞችና የሚያጠቡ እናቶች ሲሆኑ ተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ ሲያስፈልጋቸው፤ ሌሎች ከ10.5 ሚሊዮን የሚልቁት ደግሞ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ይሻሉ ተብሏል።

ኦቻ(OCHA) ለርሀቡ መባባስ እንደምክንያት የጠቀሳቸው ኢትዮጵያ ድሃ ሀገር መሆኗ፣ ድርቅ መከሰቱ፣ የበሽታ ወረርሽኝ፣ የበልግ ዝናብ በአገሪቱ ደቡባዊና ምስራቃዊ ክፍሎች አለመዝነብና መፈናቀል ዋና ወናዎቹ መሆናቸውን ዘርዝሯል።

LEAVE A REPLY