‎የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከህንድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር መጋጨቱ ተገለጸ

‎የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከህንድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር መጋጨቱ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ቦይንግ 767 የበረራ ቁጥሩ ET687 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከኒውደህሊ አዲስ አበባ ለመደበኛ በረራ ሲዘጋጅ፤ ቆሞ ከነበረ A320 የህንድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር ትናንትና ሌሊት መጋጨቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

ትናንት ማምሻውን በህንድ የኢንድራ ጋንዲ አውሮፕላን ማረፊያ ለመነሳት ወደ መንደርደሪያ ያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ክንፍ -ለክንፍ ከህንድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር መግጨቱን የህንድ ባለስልጣናትም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ጉዳት የደረሰበትን A320 አውሮፕላን “በአቬሽን ህግ” መሰረት አስፈላጊውን ጥገና በእራሱ ወጭ እንደሚያደርግ ገልጿል። መንገደኞችንም ይቅርታ ጠይቋል።

LEAVE A REPLY