ወደ ባህር ዳር የሚገባሆም ሆነ የሚወጣ ይፈተሻል

ወደ ባህር ዳር የሚገባሆም ሆነ የሚወጣ ይፈተሻል

ባህር ዳር ውጥረቱ ወጥረቱ ተባብሷል

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ባህርዳር ከተማ ውጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል። ወደ ከተማዋ የሚገባን ሆነ የሚወጣ ይፈተሻል። ነጋዴዎችንና የከተመዋን ወጥቶች በገፍ ማሰሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሱቆችም እየታሸጉ ነው። ከተመዋ በመንግስት ደህንነትና በልዩ ሀይል ፖሊስ ተጨናንቃለች።

ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ለመክፈት ቡሞክሩም ሰሞኑን “ለአድማ” ስለዘጋችሁ ዛሬም አትከፍቱም ተብለው በፖሊስ ተባረዋል።ትናንት ቀበሌ 6 (መናኸሪያ አካባቢ) ያሉ ሱቆች በሙሉ ታሽገዋል።

መንገድ ላይ አሮጌ ልብስ የሚሰፉ፤በኮንቲነር ትናንሽ የሸቀጥ እቃ የሚሸጡ ሳይቀር እስከ 30000 የስራ ግብር ተጥሎባቸዋል።የከተማው ግብር ሰብሳቢ ቡድን “የግብሩን መጠን” ለሁሉም ነጋዴዎች አላሳወቀም።”ይህም ነጋዴው አንድ ላይ ሆኖ መብቱን እንዳይጠይቅ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።ይሁን እንጂ ህዝቡን የሚለያይ አጀንዳ ከእንግዲህ አይኖርም።” በማለት መረጃውን ከባህር ዳር ያደረሰን ምንጫችን ገልፆልናል።

የደብረ ታቦርና ወልድያ ውሎም ጸጥ ረጭ ያለ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY