የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት በባቢሌና ሀረር ከተሞች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው አለ

የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት በባቢሌና ሀረር ከተሞች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው አለ

የኢትዮጵያ መንግስት ሀሰት ነው አለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሀረርና ባቢሌ መካከል ጦርነት እየተካሄደ በመሆኑ ወደ ጅጅጋና ሀረር የሚወስደውን መንገድ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ዘግተውታል።አሜሪካውያን ወደ እነዚህ ቦታዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት ትናንትና ያወጣውን የጉዜ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ መንግሥት መቃወሙ ተሠማ።

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ “ኤምባሲው ትናንት ያወጣውን ማስጠንቀቂያ ሀሰት ብለውታል።” ሲል የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘግቧል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያው ላይ ሁሌም አሜሪካውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቀሳቀሱ መረጃዎችና ዜናዎችን እንዲያዩ እንዲሁም አካባቢያቸውንም በንቃት እንዲከታተሉ መክሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ በምሥራቃዊ የኢትዮጵያ አካባቢ ምንም የተዘጋ መንገድ እንደሌለና ግጭትም እንዳልተፈጠረ በመናገር የኤምባሲውን ማስጠንቀቂያ እንደተቃወሙት ዘገባው አመልክቷል።

ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ሀሰት ነው ይበሉ እንጂ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ መንገዶች እንደተዘጉና ጠንካራ ውጊያ እንደነበረ ሀረር የሚገኙ ምንጮች ነግረውናል።በርግጠኝነት በናገር ባይቻልም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ ከኦሮሞ ታጣቂዎች ጋር በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ ይደረጋል፤ አሁንም የእዚያ አካል ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አካፍለውናል።

በሀገሪቱ ላይ የጎሳ ፌደራሊዝም ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በተለያዩ የክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በርካታ ግጭቶች ተካሂደዋል።ኦሮሚያ ክልልም ከሶማሌ፣አፋር፣ጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ጋር በተያየ ጊዜ ግጭቶች ተፈጥረዋል።

LEAVE A REPLY