የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ባለውለታን እንታደገው /ሠሎሞን ለማ ገመቹ/

የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ባለውለታን እንታደገው /ሠሎሞን ለማ ገመቹ/

በኢትዮጵያ ነፃ ፐሬስ ለረጅም ዓመታት የሠራው ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ፤ በደረሰበት አሳሳቢ የጤና ችግር ምክንያት አንድ እግሩን አጥቷል፡፡ የግራ እግሩን ከጉልበቱ በላይ ባይቆረጥ ኖሮ ሕይወቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ሊያልፍ ይችል እንደነበር በሐኪሞች ተነግሮታል፡፡ አንድ በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ ባስያዙለት 10 ሺ ብር በተዘነአ ሆስፒታል ሕክምናውን በመከታተል ላይ የሚገኘው ግርማዬነህ ቁስሉ እስኪጠግለት በሆስፒታሉ ይቆያል።

ከሐምሌ 28 – ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሆስፒታሉ ለቆየባቸውና ለሚቆይባቸው ጊዜያት፤ የሚከፍለው ከ30 ሺ ብር በላይ የሚሆን የሕክምና አገልግሎት ወጪ እንዴትና በማን ሊሸፈን እንደሚችል ብቻ ሳይሆን፤ ምንም ዓይነት ገቢ የሌለው ከመሆኑ አኳያ ወደፊት ለአርተፊሻል እግርና ለክራንች የሚሆነውን ገንዘብ ከየት ላገኝ እችላለሁ የሚለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሆኖበታል፡፡

ግርማዬነህ በአቶ ክፍሌ ሙላት ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበር አባል ሲሆን፣ በሕዝብ ዘንድ ተነባቢና ተወዳጅ መሆን በቻሉት የኢትኦጵና የዓባይ ጋዜጣና መጽሔት ዝግጅት ክፍል ከፍተኛ የዘጋቢነትና የአዘጋጅነት ድርሻውን ሲወጣ የቆየ መንፈሰ-ብርቱ ጋዜጠኛ ነበር፡፡

የጦማር ዋና አዘጋጅ ሳለ በጋዜጠኝነቱ የተነሳ ለአንድ ዓመት የታሰረው ግርማዬነህ… በጉራማይሌ፣ በኢትዮ ታይም፣ በታዛቢ፤ በትውልድ፣ ሐምራዊና ዕንቁ ጋዜጣና መጽሔቶች ሠርቷል፡፡
በአንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ከዶክተር ታዬ ወልደሰማያት ጋር በመሆን የመምህራን ማኅበሩን ልሳን ያዘጋጅ ነበር፤ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና ከሟቹ ዶክተር መኮንን ቢሻው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከልና በማጋለጥ ረገድ የበኩሉን ዜግነታዊ ድርሻ ተወጥቷል፡፡

ግርማዬነህ በተዘነዓ ሆስፒታል ሕክምናውን በመከታተል ላይ የሚገኝ ሲሆን ምንም ዓይነት ገቢ የሌለው በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ወገኖቹን ዕርዳታ ይፈልጋል፡፡ ጋዜጠኛ ግርማዬነህ ማሞ ከ1983 ግንቦት ወር በፊት የኢትዮጵያ ሠራዊት ባልደረባ ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ግርማዬነህ እግዚአብሔር ይማርህ! ማለት ለምትፈልጉ፡-
በስልክ ቁጥር 0911 12 25 29 ወይም በባለቤቱ በሽብሬ ጥሩነህ በ09 20 00 74 16 ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡
ግርማዬነህን ለመርዳት፡-
ወይዘሮ ሽብሬ ጥሩነህ አቢሲኒያ ባንክ አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ የአካውንት ቁጥር 1749501001155 በሚለው ይጠቀሙ፡፡

LEAVE A REPLY