ጎንደር ኮስተር በል! ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ-ቁ. 12

ጎንደር ኮስተር በል! ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ-ቁ. 12

ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ በተለይ ደግሞ የታሪክ ራስ የሆነችዋን መሰረት ለመናድ በጎንደር ሕዝብ እና በታሪካዊ ቅርሶቿ ላይ ጦርነት ካወጀ፤ የዘር ማፅዳት እርኩስ ዘመቻውን የክተት አዋጅ ካወጀ እነሆ ከአርባ ዓመት በላይ እያስቆጠረ ይገኛል። የባሩድ ሽታ ካልዋጀው የከባድ መሳሪያ ድምጽ ጆሮውን ካላደናቆረው መሽቶ የማይነጋለት የጥፋት መልክተኛው ወያኔን ለአገር መረጋጋት ለህዝብ ደህንነት ሲባል በሰላማዊ መንገድ ከጥፋት ጎዳናው ለመግታት እና የጋራ አገራችን ካለችበት አንስቶ ለማስቀጠል በድርጅትም ይሁን በስብስብ ከምርጫ ፉክክር እስከ ሰላማዊ ድርድር በለጋሽ አሳዳሪዎቹ ጭምር ያልተሞከረ የሰላም ድርድር የለም።

(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)
ሆኖም ብዙ አጋጣሚዎችን በድርቅና ደርቆ አድርቋቸዋል። ይሆናል ያልነውን እንደማይሆን ከነገረን ከምርጫ 1997 ዓ. ም ጀምረን እንኳ ወራት እና አመታትን ብናሰላ፤ ከአሥራ ሦስት ዓመት በላይ ቆጥረናል። እየተደራደረ መግደልን የተካነው የወያኔው ደናቁርት ቡድን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የጠበበውን ለማስፋት፤ የጠበቀውን ለማላላት ከመቅጽበት ባንኖ “ድርድር፤ ሽምግልና” እያለ አከርካሪዋን ሰብሬዋለሁ ብሉ በሚሳለቅባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቄስ መነኩሴዎች በኩል ጭምር መስቀል አሽክሞ የማይሆነውን ለመሆን ሲዋዥቅ ማየታችን የአንዴና የሁለቴ ክስተት ብቻ አይደለም።

የሰሞኑ አይሉት የጦርነት፤ ወይም የሰላም ጉግ ማንጉግ የመቀሌው “ሕዝብ የማረጋጋት” ከጎንደር እና ከወሎ በተውጣጡ ስልጡን ካድሬዎች የተሰራው ድራማ የተለመደውን ከጭንቅ መተንፈሻ የእቃ እቃ ጨዋታ ውጭ ልዩ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም። ወያኔ ለንደን ላይ ከደርግ ጋር እየተደራደረ ከመደራደሪያ አዳራሹ ሳይወጣ ከጎጃም እና ከወሎ ተንደርድሮ በቀናት ውስጥ ምንሊክ ቤተ መንግሥት ገብቶ የድል ነጋሪት መጎሰሙን አንዘንጋ! የአሁኑን የመቀሌ ሕዝባዊ ግንኙነት የማጠናከር ድርማ እየሰራ በሌላ በኩል ጦም አድረው የኑሮ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ራሳቸውን ለመጠበቅ የገዙትን የጎንደር እና የጎጃምን ገበሬዎች ትጥቅ ለማስፈታት በየአቅጣጫው ጦሩን አዝምቷል። በብዙ አካባቢዎች ለገብያ ወደ ከተማ የሚገቡ የሚወጡትን ገበሬዎች ትጥቅ ለመቀማት ሞክሯል። በምዕራብ ጎንደር በቋራ እና በሰስሜን ኮንድር በወገራ ገበሬዎች ላይ በድንገት ደፈጣ በመጣል “ክንዴን ሳልንተራስ ትጥቄን ከትክሻየ አላወርድም” ያሉ ጀግኖቻችንን ህይወት ቀጥፏል።

በሌላ በኩል ለነሱ እስከተስማማቸው ድረስ አገር እና ህዝቡን ያሻው ቢያደርግ ደንታ ያልነበራቸው የለጋሽ ነብስ አሳዳሪ አገሮች፤ አንዳንዶቹ በራሳቸው የአሰተዳደር ለውጥ ምክንያት፤ ሌሎቹ የወያኔው ግፍ እና በደል ሊደበቅ ከማይችለው በላይ በመድረሱ ምክንያት የሚሰጡትን ጉርሻ መመጠን በመያዛቸው ካዝናው እየደረቀ የመኖር ተስፋው እየተመናመነ በምጣቱ ምክንያት “ሙት ይዞ ይሞታል” እንዲሉ ሁሉንም ማህበረሰብ ይዞ ለመሞት የገብያ አቅርቦትን ለማድረቅ፤ ያላበላውን ለማስተፋት በድኃው ነጋዴ ላይ አይከፍሉት እዳ ቆልሏል። ይህን ያልታሰበና ያልተሰላ የእዳ ሸክም መክፈል የማይችሉት ነጋዴዎች ያቀረቡትን የሰላማዊ ጥያቄ በካድሬዎቹ ጠቋሚነት በደህንነቶቹ አፋኝነት በማሰር እና የማይከፈል የገንዘብ ቅጣት በማሸከም ነግዶ እና ባጃጅ ነድቶ የሚኖረውን በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደር ሕዝብ እያዋከበ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በእጁ ላይ ያለውን ማስላት መጭውን መገመት የተሳነው ወያኔ መራሹ ግትር መንግስት ተብየው የጥቂት ዘረኞች ቡድን ይህንም አድርጎ ሁኔታዎችን መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ መድረሱን በማየቱ የትግል እሳቱ እጅግ የተቀጣጠለባትን የጎንደር ክ/ሀገር በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ስም ከሶስት በመቆራረጥ በልዩ ወታደራዊ ኮማንድ ሥር አስገብቶ ለመጨፍጨፍ ተዘጋጅቷል። ለዚህም ተጨማሪ ጉልበት ያገኝ ዘንድ ለዘለዓለም በማንነታቸው ይጠሩ የነበሩትን የቅማንት ማህበረሰብ “ቅማንት አይደላችሁም” ሲል ከኖረ በኋላ አሁን ደግሞ ከሆድቻው የገባ መሥሎት፤ በሰላም እና በውህደት እየኖሩ ካሉት ማህበረሰብ ጋር ለማዋጋት ሌላ የግዛት ቀጠና በስማቸው ሊመሰርት እየጎነጎነ ይገኛል።

አስገራሚው ነገር ግን፤ በወያኔ ጥርስ የሚያላምጠው በአማራው ስም የሚነግደው የብአዴን በድን ድርጅት “ቁሜልሃለሁ” ለሚለው ህዝብ እና “አስተዳድረዋለሁ” ለሚለው ክልል ሰላምና እጣ ፈንታ አንዳችም አይነት የኃላፊነት ስሜት አለማሳየቱ በአማራው ክልል ምንም አይነት ወሳኝነት የሌለው በአማራ ስም የተቀባ የወያኔ ሌላው ጥርቅም መሆኑን ስናማ ብንቆይም አሁን ግን በገሃድ ቁርጣችን ማወቃችን ነው።

ይህ በልማትና በመልካም አሥተዳደር ስም የአገሪቱን የግዛት ዞኖች እንደገና የማዋቀሩ ሂደት በጎንደር ብቻ የሚገደብ አይደለም። በቅርቡ ከጎንደር ቀጥሎ ሕዝባዊ ነውጡ እያሰጋው የመጣውን ደቡብ ኢትዮጵያን ጎጃም እና ወሎን በተመሳሳይ መልኩ እንደገና በዞን የመከፋፈል ሥራውን እያፋጠነ ይገኛል። ኢትዮጵያን በ39 አስተዳደራዊ ዞን የመበጣጠሱ እቅድ በቅርቡ የመጨረሻው የግባ ተመሬት ሙከራውን ፍፃሜ ላይ ለማድረስ ቀን ከሌት እየሰራ ይገኛል።

በአጠቃላይ ይህን ሁሉ አድርጎ ከሚመጣው ህዝባዊ ማዕበል ማምለጥ እንደማይችል የተረዳው ወያኔ በሁለት መንገድ አገራችን ጥፍቶ ለመጥፋት ስውር ደባውን ገኃድ እያደረገ ይገኛል።

1. በሌለና ባልተፈጠረ ምክንያት ባለበት ቆሞ የነበረውን የኢትዮጵያ ኤርትራ ድንበር ችግር ወደ ጦርነት በማስገባት፤ በዘር የተከፋፈለውን የኢትዮጵያ ጦር ብትንትኑን አውጥቶ አገሪቱን ለባዕዳን ወራሪዎች አጋልጦ መሞት፤

2. በዘር ተደራጅተው ውስጥ ውስጡን እያደቡ ያሉ ከፋፋይ የጎሳ ድርጅቶች አጋጣሚውን ተጠቅመው አገራችን ኢትዮጵያን ወደ እማይጠፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዲዘፈቁ ማድረግና በዓለም ዙሪያ ያጣውን ተቀባይነት ለጊዜውም ቢሆን በማረጋጋት እና በሰላም ስም ትንሽ እድሜን ማግኙት የሚያስችሉትን ተንኮሎች መጎንጎን ነው።

ከዚህ በላይ የተጎነጎኑትን አጥፍቶ አጥፊ ተንኮሎች የበታች ካድሬውዎቹ ጭምር ጠንቅቀው በማዎቃቸው ምክንያት በልተው ለመጥፋት የአገሪቱን የገንዘብ አቅም በመሟጠጥ ላይ በመሆናቸው፤ በየትኛውም የመንግሥት መዋቅር ሳያላምጡ እየዋጡ ካዝናዎቹን ሙሉ በሙሉ እያደረቋቸው ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ እያለቀ በመምጣቱ ህጋዊ ያልሆነ የወረቀት ገንዘብ በማሳተም በጎንደር እና በጎጃም ክ/ሀገሮች የአርሶ አደሩን መሳሪያ በግዥ ስም ለመግፈፍ ለአንድ መሳሪያ መቶ ሺ ብር በመመደብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ድብቅ ስልጡን የመሳሪያ ገዥ ቡድኖችን አሰልጥኖ በትኗል። ትጥቅህን ከትክሻህ ከወረቀት በተሰራ መቶ ሺ ብር ማስረከብ፤ ሚስትህን ከክንድህ አይንህ እያየ ለሌላ እንደመስጠት ያስቆጥራል።

እናም! የጎንደር ሕዝብ ሆይ! በየጊዜው በሽማግሌ ስም እየተደራደረ ከጉያህ ልጆችህን እንደ ተኩላ እያነቀ የት እንዳደረሳቸው አንተው ታውቃለህ! ዘመድ ሳይቀር በገንዘብ እየገዛ እርስ በርስ እያባላህ እያየህ ነው። የለማ መሬትክን በጉልበት ነጥቆ፤ የቀረችዋን ለሱዳን አሳልፎ ሰጥቶ ተወላጁን ከመሬት በታች እያስረጀ፤ የቀሩትን ተሰዳጅ አድርጓል። መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ የጠየቁትን ሴቶች ሳይቀር ዘመድ ከማይጠይቃቸው ወሬያቸው እማይሰማበት ከቤተሰብ አርቆ እስር ቤት እያማቀቅ፤ በሌላ በኩል በሰላም ሽምግልና ስም ከውስጥህ የበቀሉ ሆድ አደር ካድሬዎችን የውሎ አበል እየከፈለ መቀሌ ድረስ ወስዶ በመብትህ እና በማንነትህ ላይ ሲቀልድ ማየት እጅግ ስድብም ውረደትም ነው።

ድሮውንም ቢሆን በታሪክህ በኢትዮጵያ የግዛት ዘመናቸውን ከቤተ መንግሥት ሳይወጡ በድሎት እና በቅንጦት ያለፉ መንግሥታት የሰሩትን ግፈ በድፍረት እና በቆራጥነት በመመከትህ “ጎንደር ኩራቱ ማንነቱ፤ አንድነቱ፤ ነፃነቱ” እየተዘመረልህ ዘመናትን ተሻግረሃል። ያን ታሪክህን ጠንቅቀው የሚያውቁ የዛሬዎቹ የወያኔ ግፈኞች የጥቃት ስልት ደግሞ እጅግ በተንኮል የተሞላ ነው። በፊት ለፊት ቢመጡ ሊያጠቁህ አለመቻላቸውን በመረዳታቸው ምክንያት በውስጥህ ከአብራክህ የወጡትን ጥቂት ሆድ አደሮችን በመመልመል በመሃልህ አሥርገው በማስግባት እርስ በርስ በማባላት ከእርቀት ሆነው በደስታ መፈንደቅ ነው። ቢሆንም፤ ሆዳም እና ሥግብግብ የዓይን ቀለሙም ትንፋሹም ልዩ ነው! ሳያጠፋህ የተላከበትን ጉዳይ ሳይፈጽም ቀድመህ በማጽዳት “ጠላት እማ ምንጊዜም ጠላት ነው፤ አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው” ልማዳዊ መዝሙርክን በመዘመር ከግፈኛው ሥራዓት ለአንዴና ለመጨረሻ አገር ሳያጠፋ እሱኑ ለማጥፋት ለሚደረገው አገር አቀፍ ትግል የበኩልህን አስተወጾ ለማበርከት ኮስተር! ሽክፍ ማለት ባጭር መታጠቅ ወቅታዊ ግዴታህ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የምትወዳት እና ለዘመናት ነፃነቷን ጠብቃ የኖረችው መመኪያ አገርህ ከአንድ ጎሳ በወጡ ጥቂት ብልጣ ብልጥ ቡድኖች ከመቸውም በላይ አደጋ ላይ ወድቃለች። የዘር ፖለቲካ ለ26 ዓመታት አገራችን በማድቀቁ አንድነታችን የሞተና የተቀበረ የመሰላቸው ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች በቆሰልንበት ላይ ጨው ነስንሰው፤ በተቃጠልንበት ላይ ቤንዚን አርከፍክፈው የማትነሳ እና የማትወሳ አገር እንድትሆን የቻሉትን ሁሉ ለማድረግ እየጣሩ ይገኛሉ። ለነዚህ ጠላቶችህ አሳልፎ ለእጅ መንሻ የሰጠህ ደግሞ አገር በቀል ጥቁር ሞሶሎኒ የወያኔው ጥቂት ቡድን መሆኑን ጠንቅቀህ ታውቃለህ!

በመሆኑም! ከማዶ ጠላት ጋር የተስማማን ጠላት ከቤትህ አስቀምጠህ፤ ከማዶ የመጣን ጠላት ለመመከትም ሆነ ለማሸነፍ ፈጽሞ የማይቻል፤ የማይታሰብ መሆኑን ተረድተህ አገርክን ከወራሪ ራስክን ከመሰሪ የውስጥ ጠላት ለመመከት ከመቸውም በላይ የፖለቲካ ልዩነትክን አቻችለህ በዲሞክራሲያዊ ሥራዓት መመሥረት ተማምነህ ሰባዓዊ መብት ሳይከበር የቡድን ነፃነት እንደማይኖር ተረድተህ በቅድሚያ መጠሪያ አገርክን ከተጋረጠባት አደጋ ተከላክለህ ማንነትክን ለማስከበር እጅ ለእጅ ተያይዘህ እንድትነሳ ባለፉት የነፃነት አባቶችህ ስም አደራ እንልሃለን!!

ተቃዋሚ የፖለኢትካ ድጅቶች ሆይ! ማጥፋት እንጂ ማልማት፤ ማተራመስ እንጂ መምራት ያለመደበት የወያኔው መንጋ ሕዝባችን እንደ አሻሮ እያመሰ፤ መመኪያ አገራችን እያፈረሰች ባለበት ወቅት ላይ መድረሳችን ለማንኛችሁም ልናረዳ እንዳዳም። ይሁን እንጅ የወያኔን የግፍ ዘመን ማስቀጠል ፈጽሞ አልችልም እያለ ያለው ወገናችን ያለመሪ ድርጅት ብቻውን እየተዋደቀ፤ የውጭ መንግሥታትም ወያኔን ማቀፍ እና መደገፍ ውርደት መሆኑን በተረዱበት ወቅት ላይ ሆነን በናንተ በኩል ግን ለተሰፋ የተሰነቀ አንድም ዓይነት ዝግጅት አለማየት ደግሞ እጅግ አሥገራሚ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ጭምር ሆኖ እያየን ነው። ሜዳ ሳይኖር ኳስ ጨዋታ እንደሌለ ሁሉ፤ አገር ሳይኖር ሥልጣን እሚባል ነገር ፈጽሞ ሊኖር አይችልም! የብዙ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ቅዥት ግን ከአገር በላይ ሥልጣን ሆኖ ከግል የፖለቲካ ፕሮግራም ራቅ ብሎ የሕዝባችን መከራ የሚጋራ እና የአገራችን አደጋ ቀዳሚ መፍትሔ ያደረገ መሪ ድርጅት እያየን ባለመሆናችን እጅግ አዝነናል።

በመሆኑም የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እንደ ብዙኃን ድርጅት የአገራችን የፖለኢትካ ችግር ሊፈታ የሚችለው በሁሉም አገራዊ ለውጥ እና ዲሞክራሲያዊ ነፃነትን በሚሹ የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር (ሕብረት) መሆኑን በመገንዘብ፤ ቀን እና ሌሊት ሳይቆጠርለት በተቻለ ፍጥነት በጋራ በመቆም በለውጥ ማዕበል ውስጥ እየቀዘፈ ያለውን

ሕዝባችንን ለፍፃሜ እናበቃው ዘንድ ቀን ከሌት በወያኔ ጥይት እየተጨፈጨፈ፤ በቁሙ በየእስር ቤቱ እየተሰቃየ ባለው ሕዝባችን ሥም እንማፀናለን!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት!

03/16/2017

LEAVE A REPLY