/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስጣን በአመቱ መጨረሻ ባደረኩት ፍተሻ በታክስ ማጭበርበር፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን ህጉ በማይፈቅደው መልኩ መጠቀም፣ ለቀረጥ ነፃ የተሰጠ መብትን ያለ አግባብ መጠቀምና ሌሎችንም ህገ-ወጥ ተግባራት ፈፅመዋል ያላቸውን ከ1450 በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አብዛኛውን እርምጃ የወሰደው በባህር ዳር ከተማ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። መንስኤውም ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ “ሰማዕታትን ለማሰብና ከአቅም በላይ የተጣለውን የግብር ተመን” በመቃወም ለቀናት የዘለቀ የስራ ማቆም አድማ በመደረጉ የተወሰደ የበቀል እርምጃ ነው በማለት የእርምጃው ሰለባ የሆኑ ነጋዴዎች መረጃ ሰጥተውናል።
በባህር ዳር ከተማ “በተደረገው የስራ ማቆም አድማ” ምክንያት በርካታ የንግድ ድርጅቶች ሲዘጉ ነጋዴዎችና የከተማው ወጣቶችም የእስራት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ይታወቃል።