ጊዜው 1929 ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ዳግም በወረረችበት ወቅት ነው ። ራስ ካሳ ሀይሉ ጎንደር ደብረታቦር ካለው ማዘዣ ጣቢያቸው የክተት አዋጅ አስነግረው ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ወራሪው ጣሊያንን ለመመከት እየተመሙ ነው። ራስ ካሳና ሰራዊታቸው ከደብረታቦር ተነስተው የጣሊያን ሰራዊት ወደ ሰፈረበት ትግራይ ሲጓዙ አንድ አውሮፓዊ ፈረንጅ ጋዜጠኛ አብሮ ነበር ።
ይሄ ከራስ ካሳ ሰራዊት ጋር ወደ ሰሜን የሚጓዝ ፈረንጅ በሰራዊቱ ውስጥ አንድ በእጁ የያዘው ዱላ ከቁመቱ የሚበልጥ ትንሽ ልጅ ከሰራዊቱ ጋር ሱክ ሱክ እያለ ሲጓዝ ይመለከታል።
…
የልጁ ሁኔታ ቀልቡን የሳበውና ከራስ ካሳ ሰራዊት ጋር ጦርነቱን ለመዘገብ ሲጓዝ የነበረው አውሮፓዊ ጋዜጠኛ ወደ ልጁ ይሄድና
ወደ የት እየሄደ እንደሆነ ይጠይቀዋል ።
…
ልጁም ” ጥሊያንን ልዋጋ ነው ” ይለዋል ።
…
ፈረንጁም ~ ” ጣሊያንን የምትዋጋበት ጠመንጃህ የት አለ? ” በማለት ይጠይቀዋል።
…
ልጁም ” ያችን ከቁመቱ በላይ የምትሆን ቅባት የጠገበች የወይራ ሽመል ያሳየዋል ።”
…
ፈረንጁም ፈገግ እያለ ” በዚህ እንጨት ነው ጣሊያንን የምትዋጋው? ” በማለት መሳቅ ይጀምራል ።
…
ልጁም በፈረንጁ ሳቅ ሳይቆጣ ረጋ በማለት ” ጌታው ” አለ ” ጌታው! ልብ በል ይችን ሽመል አየሃት አይደለም? በዚች አንተ እንጨት ብለህ በናቅሃት ዱላዬ መሬቴን ሊወርር የመጣውን ጣሊያንን ተዋግቼ መሳሪያውን ማርኬና ታጥቄ ላሳይህ ቃል እገባለሁ ። ” የሚል መልስ ሰጥቶት ከአጠገቡ ይሰወራል ።
…
ፈረንጁና ያ ትንሽ ልጁ ይሄን ከተባባሉ ወራት አለፋቸው። በዚህ መካከል ብዙ ጦርነቶች ተደረጉ። የኢጣሊያ አውሮፕላኖች የመርዝ ጋዝ እንደ ሀምሌ ዝናብ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ሲያዘንቡት ከረሙ። የትግራይ ባንዳዎችም ደሙን ጠብ አድርጎ አጥንቱን ከስክሶ አገሩን ሊጠብቅ የሄደውን ጦር ከጣሊያን ጋር በማበር ሲወጉት ከረሙ።
…
ከእለታት አንድ ቀን ትግራይ ተንቤን ተራራ ስር አውሮፓዊው ፈረንጅ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተዋጊዎች ጋር ድንኳኑ ደጅ ቁጭ ብሎ ጣሊያን ወደመሸገበት ተራራ እየተመለከቱ ይነጋገራሉ። በሩቅ ሲመለከቱ ትከሻው ላይ ማእረግ ያለበት የጣሊያን ዩኒፎርም ጃኬት የለበሰና መሳሪያ የታጠቀ ሰው ወደ እነሱ ሲመጣ ይመለከቱታል።
ወደ እነሱ የሚመጣው ባለመአረግ “ጣሊያናዊ ” መኮንን የለበሰው ጃኬት ሰፍቶት እንደ ካቦርት እየጎተተው መሆኑ ገርሟቸዋል። እነሱም መልእክት ይዞ የመጣ ጣሊያናዊ መስሏቸው በተጠንቀቅ እየጠበቁት ነው። ወደ ድንኳኑ እየቀረበ ሲመጣ ጣሊያናዊ ሳይሆን መልኩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን እያረጋገጡ ነው። በመጨረሻ ድንኳኗ አጠገብ ሲደርስ ያ ከደብረታቦር ከቁመቱ በላይ የሆነ ዱላ ይዞ የዘመተው ትንሹ ጎንደሬ ልጅ ነው። እርግጥ ነው መጀመሪያ ደብረታቦር ላይ ሲታይ እንደነበረው አይደለም ። ጎስቆልና ጠቆርቆር ቢልም አሁንም የልጅነት ወዙ እንዳለ ነው።
…
ልጁ ቃል በገባው መሰረት በዛች ዱላ የጣሊያን ሻለቃ ጥሎ መሳሪያውን ከነዩኒፎርሙ ገፎ ከአሳየው በኋላ ብዙም ሳያነጋግረው አሁንም ለሌላ ጀብዱ ከፊቱ እንደተሰወረ ፈረንጁ ፅፏል። አውሮፓዊው ትረካውን ሲቀጥልም……<< አሁን የመሳቁ እና የማሾፉ ተራ የጎንደሬው ትንሹ ልጅ ተራ ነበር ። በእኔ በኩል በድንጋጤ፣ በመገረም እና በአድናቆት የከፈትኩትን አፌን መልሼ ሳልዘጋው ትንሹ ልጅ ከአጠገቤ ሽው ብሎ ጠፋ ይላል።
…
ዛሬ ከ 80 አመታት በፊት በትንሹ ጎንደሬ ልጅ የተሰራውን እና በአይን ምስክር የተፃፈውን ገድል አስታውሼ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ በአገር በቀል ፋሽስት በሆነው ወያኔ ጎንደር ላይ እየተቀበረ ያለውን ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ ( Time Bomb) ሁሉም እንድገነዘበው አፅንኦት ለመስጠት ነው። ህውሃት ገና ከጥንስሷ ጀምራ አማራ ላይ የምትከተለው ፖሊሲ ከጣሊያንና ከእንግሊዝ የተቀዳ ፖሊሲ ነው ። ይሄን መርዘኛ ፖሊሲ Anglo _Italo policy ልትሉት ትችላላችሁ ።ይሄ ፖሊሲ አንድ ወጥ ፖሊሲ ሳይሆን ከሁለቱም አገሮች አደገኛ አደገኛው ፖሊሲ ተመርጦ የተዘነቀበት ነው። ታርጌቱ አማራ ነው። የዚህን ፖሊሲ እጅግ አሰቃቂ የሆነውን Collateral Damage ወደ ፊት የምንመለከተው ይሆናል። አሁን ጊዜው ገና ነው።
…
የዚህ መርዘኛ ፖሊሲ አርክቴክቶች ከጣሊያንና ከእንግሊዝ ጋር ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምሮ ዝምድና ያላቸው ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ናቸው።
እንደሚታወቀው የስብሃት ነጋ ቅድመ አያት እንግሊዛዊ ነው ። የስብሃት ነጋ አያት በሮበርት ናፔየር እየተመራ በአፄ ዮሃንስ ጓዝ ተሸካሚነት መቅደላ ላይ ቴዎድሮስን ወግቶ ሲመለስ መቀሌ እረፍት ሲወስድ ለእንግሊዝ ወታደር የጭን ገረድነት ከተመደቡ ሴቶች የተወለደ ሰው ነው። እንግሊዛዊው ወታደር መቀሌ ላይ ዘሩን ብቻ ሳይሆን ጥሎ የሄደው እንግሊዛዊ ተንኮሉንና የአማራ ጥላቻውንም ጭምር ነው። ስብሃት ነጋ ከእንግሊዛዊ አያቱ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ በህዝቦች መካከል መቅበርመቅበር በለመደው መሰረት አማራ ላይ እየተገበረው ይገኛል ።
የመለስ ዜናዊ አባትና አያት ደሞ የኢጣሊያ ባንዳ ናቸው። አያቱ የጣሊያን ፌርማቶሪ የነበሩ ሲሆን አባቱ ደሞ ለጣሊያን በመላላክ ያገለግሉ ነበር። ልብ በሉ ህውሃት በአማራ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ የቀረፁት እነዚህ ሁለት ሰዎች ናቸው። የእንግሊዛዊው ወታደር የልጅ ልጅና የጣሊያናዊው አሽከር የልጅ ልጅ የፖሊሲው አባት ናቸው።
…
አሁን በተጨባጭ በአማራ ህዝብ ውስጥ የሽንፈት ፅዋውን እየሰረገበ ያለው ህውሃት በአማራ ክልል በሚኖሩ ህዝቦች መካከል ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ ለመቅበር ዙሪያውን እየቆፈረ ነው። ይሄ ታይም ቦምብ ስሙ ” በጎንደር ቅማንት ልዩ ዞን ” ይባላል። ይሄ እጅግ አደገኛ ቦምብ ነው ። አማራና ቅማንት ከ3000 አመታት በላይ በፍቅርና በሰላም አብረው የኖሩ ህዝቦች ናቸው ። አሁን ግን በመካከላቸው አርማጌዶን ለመፍጠር ቦምብ እየተቀበረባቸው ይገኛል።
የጣሊያኑ ከፋፍለህ ግዛና የእንግሊዙ ታይም ቦምብ በህውሃት አርክቴክትነትና በብአዴን ተላላኪነት አማራን የአኬልዳማ መሬት ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል። ይሄ እኩይ ሰይጣናዊ ተግባር መቼም እውን አይሆንም ። አማራ በሰላም ጊዜ ገበሬ በክፉ ቀን ነፍጠኛ ነው። መሬት ፣ነፍጥና ሞፈር የአማራ የህይወት መሰረት ነው። አማራ በመሬቱ ድርድር አያውቅም።
ከ80 አመታት በፊት የጎንደሬው ትንሹ ልጅ መሬቱን ሊቀማ የመጣውን ጣሊያናዊ ሻለቃ በሽመል መሳሪያውን ከእነዩኒፎርሙ ገፍፎ እንዳጋደመው ሁሉ አሁንም መላው የአማራ ህዝብ ጎንደር ላይ እየተቀበረ ያለውን አደገኛ መርዝ ነቅሎ ያከሽፈዋል።