/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የክልሉ መንግስት ኮሚንኬሽ ባወጣው መግለጫ የህወሓት የመበታተን ሴራ የጎንደር ህዝብ ጥያቄ ላማስመሰል የሚከተለውን፤ “የሰሜን ጎንደር ህዝብ በተደጋጋሚ ያነሳው የነበረ ጥያቄ በልማታዊው መንግስታችን አስተዋይነት ምላሽ በማግኘቱ ሰሜን ጎንደር ዞን በሶስት ዞኖች ተደራጀ፡፡” ብሏል።አዲሱ አደረጃጀትም
1.ሰሜን ጎንደር ዞን ማዕከሉ ደባርቅ ከተማ
2.ምዕራብ ጎንደር ዞን ማዕከሉ ገንዳ ውሃ ከተማ
3.ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማዕከሉ ጎንደር ከተማ በመሆን በአዲስ ተመስርተዋል፡፡
በየ ዞኑ የተካተቱ ከተማ አስተዳደር እና ወረዳዎች
1.በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የተካተቱ ከተማና ወረዳዎች
• ደባርቅ ከተማ አስተዳደር
• ዳባት ከተማ አስተዳደር
.ደባርቅ ወረዳ
.ዳባት ወረዳ
• ጃን አሞራ ወረዳ
• በየዳ ወረዳ
• ጠለምት ወረዳ
• አዳርቃይ ወረዳ
2.በምዕራብ ጎንደር ዞን ስር የተካተቱ ከተማና ወረዳዎች
• ገንዳ ውሃ ከተማ አስተዳደር
• መተማ ዩሃንስ ከተማ አስተዳደር
• ምድረ ገነት ከተማ አስተዳደር
• ቋራ ወረዳ
• መተማ ወረዳ
• ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ
• ጭልጋ/ቆላው/ወረዳ
3.በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስር የተካተቱ ከተማና ወረዳዎች
• ጎንደር ዙሪያ ወረዳ
• ምዕራብ በለሳ ወረዳ
• ምስራቅ በለሳ ወረዳ
• ኪንፋዝ በገላ ወረዳ
• ወገራ ወረዳ
• ጠገዴ ወረዳ
• ታች አርማጭሆ ወረዳ
• ማሰሮ ደንብ ወረዳ
• አለፋ ወረዳ
• ጣቁሳ ወረዳ
• ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ
• ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በሚል ተደራጀተዋል።
ክልሉ ይህን ይበል እንጂ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ እያነሳ ነው።ህወሓት የጀመረውን የመከፋፈል ሴራ አሁንም አጠናክሮ በመቀጠል አካባቢውን በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ አቅም ለማዳከም ነው ተብሏል።