/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በምስራቅ ኢትዮጵያ በመኢሶን ከተማ አቅራቢያ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ።በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በወሰን ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት ለወራት መዝለቁ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ማምሻውን በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን ያሳተፈ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
የሶማሌ ጎሳዎች ልዩ ፖሊስ እየተባሉ በሚጠሩት በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ ወታደሮች የተደገፈ መሆኑም ታውቋል።የሶማሌ ጎሳዎች የጥፋት ሀይል በሆነው በልዩ ፖሊስ በግልፅ በመታገስ ወንዶችን እየገደሉ፣ሴቶችን እየደፈሩ እንዲሁም ከብቶቻቸውን እየዘረፉ እንደሚገኙ የመኢሶን አካባቢ ነዋሪዎች ገልጸዋል።እስካሁን በሁለት ሳምንት ብቻ በግጭቱ ከ30 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ60 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ከ15 ቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ሲያወጣ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ሀሰት ማለቱ የሚታወስ ነው።