ያልተነገረው ይነገር!… ኢሳያስ እንዴት ወደ ስልጣን መጣ? /በአብይ አበራ/

ያልተነገረው ይነገር!… ኢሳያስ እንዴት ወደ ስልጣን መጣ? /በአብይ አበራ/

አቶ ኢሳያስ አባቱ አቶ አፈወርቅ አብርሀ የተወለዱት ትግራይ ተንቤን አጋሜ አውራጃ ሲሆን እናቱ ወ/ሮ አዳነች በርሔ የተወለዱት ከአድዋ አውራጃ የይሐ መንደር ነው፡፡ አቶ ኢሳያስ የተወለደው ኤርትራ ቢሆንም የተማረው ወሎ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት ሲሆን አንደጨረሰ በአ.አ ዩኒቨርስቲ የኢንጅነሪንግ ተማሪነቱን አቋርጦ የኢትዮጵያ ደህንነት ቢሮ ተቀጠረ፤፤ በ1961 ዓ.ም ጀብሃ የተባለውን ገንጣይ ድርጅትን ያቋቋመው የግብጹ መሪ ጋማል አብዱልናሰር ነበር፡፡ እኝህ የግብጽ መሪ ጀብሐን ያቋቋሙት በዋናነት በአባይ ወንዝ ኢትዮጲያ እዳትጠቀም እና ሰላም ለማናጋት ብሎም የቀይ ባህርን ወታደራዊ ጠቀሜታውን ለመውሰድ ነበር፡፡

የጀበሀው መሪው ሆኖ የተመረጠው ኢድሪስ መሀመድም የቤንዓመር ጎሳ ተወላጅ ነበር፤፤ በፌዴሬሽን ጊዜም የኤርትራ የፌዴሬሽን ሊቀመንበር ነበር ፡፡ ጀበሐ ሲቋቋም 2000 የሚሆኑ አባላት ነበሩት ፡፡ መሪዎቹም› ኢድሪስ መሀመድ ሊቀመንበር፤ ኡስማን ሳላሳቢ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ፤ኢድሪስ አዋሴ ወታደራዊ ክፍል ኃላፊ ነበሩ፡፡

ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ስለዚህ ጉዳይ አስከፊነት ስለተገነዘቡ ይህን ሀይል ለመደምሰስ ሰላይ መላክ አለበን ብለው ከመከሩ በኃላ ኃላፊነቱን ለወቅቱ ኤርትራ ገዥ ለልኡል አስራተ ካሳ ሰጧቸው፡፡ልኡል አስራተ ካሳም ከኢሳያስ አጎት ጋር ከወሎ ገዥ ደጅአዝማች ሰለሞን አብርሃጋር በመሆን ከመከሩ በኃላ፣ ደጅአዝማች ሰለሞን አብርሐ ያሳደጉትን የወንድማቸውን ልጅ ኢሳያስ አፈወርቅ መለመሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ኢሳያስ በቀዳማይ ሀ/ስላሴ የኢትዩጲያ የውጭ ኢንቴሌጀንት በነበሩት በክቡር ብርጋዴል ጀነራል ዳንኤል መንግስቱ ስር እንዲሰራ ሆኖ ደመወዝ እየተከፈለው የኢትዩጲያ የውጭ ኢንቴሌጀንት ሆኖ ተቀጠረ፡፡
ከዛ ስልጠና ተሰጥቶት ወደ ሱዳን ተላከ ፡፡ በ1966 ዓ.ም ጀብሀኝ ተቀላቀለ፡፡ ጀብሐም ምንም ሳይጠራጠር ባባልነት ተቀብለው፡፡ ኢሳያስ በረሀ የወጣው ኤርትራን ነጻ ሊያወጣ ሳይሆን የኢትዩጲያ ቅጥረኛ ሆኖ ነበር፡፡

ከዛም ኤትርትራ በረሐ ወርዶ ጀብሐን የመሰንጠቅ ስራውን ቀጠለ፡፡ ኢሳያስ ጀብሐ ውስጥ አንድ አመት ሳይሞለው ለ6 ወር ቻይና ተልኮ ማርክሲዝም ሌኒዝም ማሆሂዝምን ሰለጠነ፡፡ከሱ ጋር አብረው የሰለጠኑትም መሀመድ ቸክሊ፣ መሀመድ ብርሀን፣ አህመድ አደም ፣ሮመዳን መሀመድ ነበሩ፡፡ ጀብሃ የእስላም ስብስብ ስለነበረ ሙሉ በሙሉ መገንጠል አልቻለም፡፡ ይሁን ኢንጂ በቡድኑ ውስጥ የተወሰኑ ሰዎችን ይዞ ሰልፊ ነጻነት የሚል ድርጅት አቋቋሞ የተወሰኑ አባላት ይዞ ሊወጣ ችሏል፡፡
የሰልፊ ነጻነት አባል የነበሩ አብርሀም ተወልደ ዋና ፀሀፊ ፤ኢሳያስ አፈወርቅ ምክትል ፤ወልደይ ግዳይ ፣ ሰለሞን ወ/ማሪያም ሙሴ ተስፋዬ ፣ኢብራሂም ሀሰን፣ ሮመዳን ሙሀመድ ዋናዋናወቹ ነበሩ፡፡ይህ ቡድን አላ ወደሚባል በረሐ ሄደ ተቀመጠ፡፡ ከዛም ጀብሀን ለመዋጋት ከኢትዩጲያ መንግስት በድብቅ መሳሪያ መሰባሰብ እና ጦር ማደራጀት ቀጠለ፡፡

ንጉሱም ኢሳያስን ጀብሐን ለማጥፋት ብቃት እንዲኖረው በአሜሪካኖች የስለላ ድርጅት እንዲሰለጥን ፈቀዱ እና ከአሜሪካው የአፍሪካ ድህንነት ተጠሪ ከሆኑት ከሪቻርድ ኮፕላር ጋር ለመሰልጠን ከአላ በረሓ በድብቅ ኢትዩጲያ እየመጣ መሰልጠን ጀመረ፡፡ ባንዳው ኢሳያስ ከሲ.አይ.ኤ ጋር በማሴር ንጉሱ ሳያውቁ የኤርትራን መገንጠል ከሚፈልጉት ከአሜሪካኖች ጋርም ተሻረከ ፡፡በመቀጠል የሰልፊ ነጻነት ፀሀፊን አብርሀም ተወልደን በመርዝ ገሎ ሰልፊ ነጻነት ዋና ኃላፊ ሆነ፡፡ ከዛም ከሰልፊ ነጻነት ድርጅቱን EPLF ብሎ ቀየረው ፡፡ ነገር ግን እሱ ሀላፊ ከሆነ ከአረብ ሀገራት እርዳታ ስለሚገኝ እራሱን ምክትል አድርጎ ሮመዳን ኑር መሀመመድን የድርጅቱ መሪ አርጎ ሾመው፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ኢሳያስ ለኢትዩጲያ መንግስትም እየሰራ ነበር፡፡ እንደውም በ1965 በኢትዩጲያ አየር መንገድ ወደ ኤደን እና ቤሩት ተጉዟል፡፡ ስለዚህ ኢሳያስ 4 ካርድ ይዟል ማለት ነው፡፡

ኢሳያስ ከአረብ አገሮች ጋር በመሆን እና ኡስማን ስላሳቤን በማሳመን እርዳታ መግኘት ጀመረ፡፡ እና ድርጅቱ ለነሱ በሚመች አርጎ ሻቢያ ብሎ ሰየመው ፡፡ ኦስማን ሳለሳቤ የስብሀት ነጋም የቅርብ ወዳጅ ነበር፡፡ ኢሳያስ ይህን ሁሉ ካደረገ በኃላ ለህዝቡ ኤርትራ ሀገር እንደሆነች፤ እንደተጨቆነች፤ አማራ ጠላቷ እደሆነ ፤50 ዓመት በጣሊያን 10 ዓመት በእንግሊዝ የተገዛነው ሀገር ስለለበነር ነው፣ አጼ ሚኒሊክ ከመረብ ወዲያ የኛ አደለም ብለዋል፣ ስንገዛ ኢትዩጲያ ምንም አላገዘችንም፤ እኛ የሰለጠንን ስለሆን ከነሱ ጋር ከተቀላቀልን ወደ ኃላ እንቀራለን እያለ ቻይና የሰለጠነውን ተንኮል ማሰራጨት ጀመረ፡፡ ቀጥሎም ወደ እናት አባቱ ሀገር ትግራይ ስር መስደድ ጀመረ፡፡

ግግሃት የተባለውን ጀብሓ ፈጥሮት የነበረውን የትግራይ ቡድን ማግብት ( ማህበረ ገሰግሲ ብሔር ትግራይ) የሚባለውን በሻቢያው መሀሪ ተክሌ አማካኝነት የካቲት 11 1967 5 ጠበንጃና 11 ጩቤ በያዙ ተጋዬች መሰረተ፡፡

መስራቾቹ
አጋዚ ገሰሰ( ዘሩ)፣ ስዩም መስፍን ( እምባየ) ፤ በሩሁን ሀጉስ( ሙሉጌታ) በሪሁ በርሔ ( አረጋዊ) ልኡል አየለ( ገሰሰ) ፤ፈንታሁን ዘ/ጽዮን( ግዲይ)፤ ኃይሉ መንገሻ( አለምሰገድ) ፤አባይ ፀሀይ ( አመሃ) ነበሩ፡፡

ሲጀመር ኢሳያስ የትግሬን ድርጅት ማግብት ትሃት ተብለው ስም እንዲወጣላቸው ቢያደርግም እነሱ ግን አሻ( ASHA) ብለው ተደራጁ፡፡ ( አደዋ ሽሬ አክሱም ) ይህ ግን የትግራይን ህዝብ አላካተተም ተብሎ ወያኔን በመጨመር ህወሃት አሉት፡፡ እኝህ ገንጣይ አስገንጣይ በ21ኛው ክ/ዘመን የተፈጠሩ ደናቁርት የጎሳ ፊታወራሪዎች አሁንም መሰሪ በሆነ አካሄድ በተቀነባበረ ሴራቸው እስከአሁን ድረስ ኢትዩጲያን እየበዘበዙ ገና ለቀጣይ አመታት በአጥንቷ እስክትሄድ ድረስ ያለእርህራሄ ለመቦጥቦጥ አዳዲስ ሴራን እያሴሩ ለመኖር ታጥቀው የተነሱ ሰው በላወች ናቸው፡፡

LEAVE A REPLY