የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ-ሶማሌ ድንበር አካባቢ የተከሰተውን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ መግለጫ አወጣ

የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ-ሶማሌ ድንበር አካባቢ የተከሰተውን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ መግለጫ አወጣ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ-ሶማሌ ድንበር አካባቢ የተከሰተውን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ መግለጫ አወጣ

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በሐረርጌ የጎሳ ግጭትን እና የበርካታ ሰዎችን መፈናቀል አስመልክቶ በሚወጡ አሳሳቢ ዘገባዎች ተረብሸናል፤ ምንም እንኳ ዘገባዎቹ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ስለማቅረባቸው ግልጽ ባይሆንም፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፤ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሹ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጠንካራ፤ የበለጸገች እና ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆን የምትችለው፤ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፤ ግልጽ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር ስትችል እንደሆነ እናምናለን፡፡ የሰሞኑ ሁነቶች በተጠቀሱ ዘርፎች ይበልጥ ፈጣን እና ተጨባጭ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ናቸው፡፡” በማለት በኢትዮጵያ የተከሰተው መጠነ-ሰፊ የጎሳ ግጭ እንዳሳሰበው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። መግለጫው በእንግሊዝኛ ከታች ተያይዟል።

LEAVE A REPLY