ይድረስ የኢትዮጵያን አገራዊ ሏአላዊነት እና ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ነፃነት ለምታስቡ የፖለቲካ እና የማህበራዊ...

ይድረስ የኢትዮጵያን አገራዊ ሏአላዊነት እና ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ነፃነት ለምታስቡ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ድርጅቶች በሙሉ

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ዝቅ ብሎ በጎንደር ከፍ ብሎ በኢትዮጵያ ሕዝብ እየደረሰ ያለውን የአገራዊ አንድነት እና የሕዝባዊ ነፃእት በደል በተከታታይ የሚሰማውን አገራዊ እና ሕዝባዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሚታገላቸው ድርጅታዊ ኃላፊነቶች ባሻገር ወጥቶ ከሌሎች በተለያየ መልኩ ለሕዝባቸው እና ለአገራቸው አስበው ከተደራጁ መሰል ድርጅቶች ጋር በተጓዳኝ ለመሥራት ያለውን ፍላጎት ሲገልጽ መቆየቱ በተደጋጋሚ ካወጣናቸው መግላጫወች እና መልክቶቻችን መረዳት ይቻላል።

ይሁን እንጅ፤ አገራችን በወሰን፤ ሕዝአባችን በነፃነት ከመቸውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ከመኖር ወደ አለመኖር እያሽቆለቆለ፤ የፖለቲካም ሆነ የማሕበራዊ ድርጅቶች ደግሞ ሊያቅፉት እና ሊደግፉት ወይም ሊመሩት የሚገባውን ያክል ተስፋ ሊስጡት ያልቻሉበትን ሁኔታ እያየን አለመምጣታችን እጅግ አሳሳቢ ሆኖ አግኝተነዋል።

ቢሆንም የነገውን ተሥፋ ብርዛሬው ሁኔታ ማጨለም የአንድ ሕዝባዊ እና አገራዊ ኃላፊነት የተሸከመ ድርጅት ቀርቶ እንደ ዜጋ በግልም ቢሆን የማይታሰብ የትግል ወኔ መሆኑን በማመን ሁላችሁም በዚህ የትግል ወኔ እልህን አጭራችሁ፤ በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን አገራችን ኢትዮጵያን ከውድቀት፤ ሕዝባችንን ከወያኔ ባርነት እንታደግ ዘንድ በሚከተሉት ወቅታሁኔታዎች ላይ እንደ ወቅታዊ የትግል መፈክር አቀናጅተን በምንችለው አቅም እንድረባረብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

1. “ኢትዮጵያን ለማፍረስ፤ ዳር ድንበሯን መቁረስ ብሎም ለባዕዳን ማውረስ” በሚል መርህ ተነስቶ ለኢትዮጵያ አንድነት መሰረት የሆነችዋን ጎንደርን ለማጥፋት ወልቃይትን ወደ ራሱ ከልሎ፤ የቀረውን ለሱዳን ገብሮ ከዚያ የተረፈውን ደግሞ ቅማንት እና አማራ ብሎ ማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር ደም ለማፋሰስ በሰዓታት እየተቆጠረ ያለውን የወያኔ ደባ በያላችሁበት በምትችሉት የመገናአኛ ብዙኃን ታወግዙ ዘንድ፤

2. በተለይ ደግሞ ከዚህ በላይ በቁጥር አንድ ላስቀመጥነው ችግረ አራጋቢ በመሆንም ይሁን ችግሩ ወደ የት አቅጣጫ እየወሰዳቸው እንዳለ በዓይናቸው መሬቱ ላይ ሆነው እየተመለከቱ በድርቅና የቅማንትን ብሔረሰብ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በዋናነት ከፊት ሆነውእየገፉ፤ ለዚህ ጥፋት ተባባሪ አንሆንም ያሉትን ተቀላቅለው በሚኖሩ ወገኖች ላይ ለወያኔ አሳልፈው በመስጠት ችግር እያደረሱ ያሉ ወገኖቻችንን በምትችሉት ሁሉ በመገናኘት ከታሪካዊ ማህበራዊ ጥፋት
እንዲታቀቡ መልክታችሁን በተማጽኖ ታስተላልፉ ዘንድ፤

3. የጎሳ ፌደሬሽን ሊያመጣ የሚችለውን የማሕበራዊ ቀውስ አበክረን ብናወግዝም፤ አይኑን ጨፍኖ’፤ ጆሮውን ደፍኖ እየቀጠለ ያለው ጉግ ማንጉጉ የወያኔው አገር አፍራሽ ቡድን በሱማሌ እና በኦሮሞ ወገኖቻችን መካከል በጫረው የደም ማፋሰስ ምክንያት እየደረስ ያለውን አገር አፍራሽ፤ህዝብ ጨራሽ ሁኔታ በጋራ ለዓለም አቀፍ መገናኛዎች፤ ለለጋሽ አገሮች ድምፃችን በማሰማት፤ ከህዝባችን ጎን መቆማችንን ገላጭ በሆነ ሁኔታ ሃላፊነታችንን እንድናሳይ፤

4. አገራችን ኢትዮጵያ ከመቸውም በላይ ከገባችብት ሁኔታ እንታደጋት ዘንድ በጋራ አብረን እና ተባብረን ለሕዝባችን በሕብረት መቆማችንን የምናሳይበትን ቋሚ የጋራ መድረክ እንፈጥር ዘንድ ህይወትን ሰጥተው ድሎትን ክደው ታሪክን በደማቸው ጽፈው ባለፉት እንቁ ኢትዮጵያውያን ስም ዛሬም እንደ ልማዳችን እንማፀናለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት።

LEAVE A REPLY