የሳሙኤል አወቀ የግድያ ቅንብር /ሙሉቀን ተስፋው/

የሳሙኤል አወቀ የግድያ ቅንብር /ሙሉቀን ተስፋው/

(ከደኅንነት ቢሮ የወጣ)

ከብሔራዊ ደኅንነት አዲስ አበባ ሳሙኤል አወቀ እንዲገደል ትእዛዝ ባሕር ዳር ላለው የደኅንት ቅርንጫፍ ተላለፈ፡፡ ባሕር ዳር ያሉት የደኅንነት ሠራተኞች ሳሙኤል ስለመገደሉ እንጅ ለምን እንደሚገደል በጊዜው የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ በሕወሓት በደኅንነት አንድን ኦፕሬሽን አለ አከናውኑ ከተባሉ ያለ ምንም ጥያቄ ኦፕሬሽኑን ማከናወን ነው፡፡

ይህን ኦፕሬሽን ለማከናወን ደረጀ አላምረው የተባለ የደብረ ማርቆስ ልጅና ቴዎድሮስ አለኸኝ በመባል የሚታወቅ ባሕር ዳር የሚሠራ የትግራይ ተወላጅ በአንድ ላይ ሆነው ነው፡፡ ደረጀ አላምረው የሚባለው ሆድ-አደር በደኅንነቱ መሥሪያ ቤት ኃላፊነቱ የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች መረጃ ኃላፊ ሲሆን ለዚህም እንዲያመቸው የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ የግል ሾፌር ሆኖ እንዲመደብ ተደረገ፡፡ ዶክተር ባይሌ ሹፌርነቱን ለቆ እስኪሔድ ድረስ ደረጀ ደኅንነት መሆኑን የሚያውቁ አይመስልም፡፡

ሳሙኤል አወቀ ቀደም ሲል ደረሰበትን ድብደባ አያይዞ ወደ ባሕር ዳር የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ይመላለስ ነበር፤ መስጊዱ ጎን ካለው የሰመጉ ቢሮ ሲወጣና ሲገባ እየተከታተሉ በተደጋጋሚ ደብረ ማርቆስ ድረስ ሸኝተውታል፡፡ የግድያው ቀን ሲወሰን ለዶክተር ባይሌ ተለዋጭ ሾፌር ተመድቦለት ደረጀ አላምረው የግድያውን ቡድን በይፋ ተቀላቀለ፡፡ እነ ቴዎድሮስ አለኸኝና ደረጀ አላምረው ኮድ 3 እና ታርጋዋ ቁጥሯ አማ- 13572 ፒክ አፕ ጥቁር መኪና ይዘው ወደ ደብረ ማርቆስ አመሩ፡፡ ከአዲስ አበባ ከመጡ አፋኝ ቡድኖች ጋር በአንድ ላይ በመሆን ደብረ ማርቆስ ተደብቀው ሰነበቱ፡፡ በሦስተኛው ቀን ምሽት ሳሙኤል አወቀን የመግደል ኦፕሬሽኑ ተጠናቀቀ፡፡

ኦፕሬሽኑ እንደተጠናቀቀ የመኪናዋ ሰሌዳ ተቀየረ፡፡ የማርቆስ ከተማ ሕዝብ በጠቆመው መሠረት ገዳያችን የያዘችው መኪና ታርጋ ከላይ የተጠቀሰው እንደሆነ ቢገለጽም ወዲያውኑ ቀይረውት ስለነበር ግድያውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባና ባሕር ዳር አመሩ፡፡ ሳሙኤልን ከገደሉ በኋላ ቴዎድሮስ የተባለው ትግሬ በሳምንቱ አዲስ አበባ ተዛውሮ ዋናው የደኅንነት መሥሪያ ቤት በኃላፊነት ቦታ ላይ ተመደበ፡፡

ደረጃ አላምረው የተባለው ደግሞ የዶክተር ባይሌ ሾፌርነቱን ሳይመለስበት ባሕር ዳር የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የአፈናና የኦፕሬሽን ቡድን መሪ ሆኖ ተመደበ፡፡ የሚያስገርመው ደግሞ ስትፈለግ የነበረችው መኪና ሰሌዳ ለሁለት ዓመታት ያክል ተደብቆ ቆይቶ አሁን ሁኔታው ተረጋግቷል ተብሎ መኪናዋ ከነሰሌደዋ ለእርሱ ተመድባለች፡፡

ደረጀ አላምረው ቤቱ እንደማንኛውም ደኅንነት ኪቤአድ ውስጥ ነበር፤ አሁን ላይ ፈርቻለሁ ብሎ በማመልከቱ ከወታደሮችና አየር ኃይል አባላት ጋር በመኮድ ግቢ እየኖረ ይገኛል፡፡ ደረጀ አላምረው የሚባለው ደኅንነት በየጊዜው ስልኩን የሚቀያይር ቢሆን አሁን የያዘው ስልክ 0918779372 ነው፡፡ በዚህ ስልክ ቫይቨር ሁሉ እንደሚጠቀምበት ለማወቅ ችያለሁ፡፡

(በነገራችን ላይ የዐማራ ሕዝብ ዋነኛ ጠላት የሆኑ ሰዎች ሥራ በሚገባ እየደረሰን ነው፤ ቀስ እያደረግን ሁሉንም እንለቀዋለን ፎቶግራፉ የደረጀ አላምረው ነው፡፡ )

LEAVE A REPLY