ለአቶ በቀለ ገርባ የፈቀደው የዋስትና መብት ታገደ

ለአቶ በቀለ ገርባ የፈቀደው የዋስትና መብት ታገደ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት ለአቶ በቀለ ገርባ የተፈቀደውን ዋስትና አገደ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተፈቀደውን ዋስትና ያገደው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቤቱታን ተከትሎ ሲሆን፥ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በማለት ነው።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግባኝ ሰሚ 1ኛ የወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ አቶ በቀለ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ትእዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።በሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት ይህ ውሳኔ የታገደ ሲሆን፥ አቶ በቀለ ገርባም መልስ እንዲሰጡ ታዟል።

ስለ ጉዳዩ አስስተያየታቸውን እንዲያካፉሉን የአነጋገርናቸው አንድ የህግ ባለሙያ “ሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት” የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ መሻር እንደማይችል አስተያየታቸውን ሰተውናል።

የሰበር ሰሚ ችሎት ስልጣን የጠቅላይ ፈርድ ቤት ውሳኔዎችን በመመርመር አስተያየት መስጠት እንጂ መሻር አይችልም ብለዋል።የፈርድ ቤት ውሳኔዎች በእስር ቤት ሀላፊዎችና በመንግስት ባለስልጣናት ሲሻር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በተለይም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ውሳኔ ሲያሳልፍም ለወራት በእስር ቤቶች እንዲያሳልፉ እንደሚደረግ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY