‎በቡኖ በደሌ ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ለመደገፍ ተከፍቶ የነበረው የባንክ አካውንት እንዲዘጋ የደህንነት...

‎በቡኖ በደሌ ለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ለመደገፍ ተከፍቶ የነበረው የባንክ አካውንት እንዲዘጋ የደህንነት ቢሮው ትዕዛዝ አስተላለፈ

/በስንታየሁ ቸኮል/

በኢሊባቡር መቱ በአማራ ተወላጅ ወገኖች በደረሰባቸው ጭፍጨፋ በጊዚያዊ በመጠለያ ካምፕ የሚኖሩ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ በሀገር ውስጥ በተቋቋመ አስተባባሪ ኮሚቴ መሠረት ሰብዓዊ እርዳታ የማሰባሰቡ ተግባር ከብሔራዊ ደንህንነት በተላከ ጥብቅ መመሪያ ምክንያት ዛሬ 22/02/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳቡ እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል አለ!”

በውስጥና በውጭ የሚገኙ ወገን ወዳድ ዜጎች ለዚህ በጎ አላማ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በአጭር ቀን ከመቶ ሺህ ብር በላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡

ይህ ሁኔታ ያስደነገጠው ስርዓት ለሌላ አላማ ገንዘቡ ይውልል በማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ የኮሚቴው ተወካይ በማስጠራት የመንግስት ከፍተኛ አመራር ጥብቅ ክትትል ስጋት ስላደረበት አካውንቱ እንዳይንቀሳቀስ ገንዘቡ እንዳይወጣ መከልከሉ በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

የባንኩ ዋና ፕሬዝዳንት የተከፈተው ሂሳብ እንዲዘጋ ወደ ፌደራል ዐቃቢ ህግ ፍትህ እንድንሄድ ትህዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ በቅርቡ ወደ አካባቢው የተጓዙ ሰዎች ተከልክለው መመለሳቸው መረጃው ተሰምቷል፡፡ ነገ ሐሙስ በሁለት የተከፈለ የልሁካን ቡድን ወደ ተጎጂ ወገኖች ዘንድ ለመሄድ ዝግጅት ጨርሰው ባለበት ሁኔታ ከመንግስት ደህንነት አካል በተላከ መመሪያ ሂሳቡ መታገዱ አግራሞት ፈጥሯል፡፡

የጉዳቱ ሰለባ ወገኖቻችን የሚረዱበት መንገድ እስኪመቻች ድረስ በተከፈው ሂሳብ ቁጥር 1000224158223 በመንግስት ጫና መዘጋቱን ለመላው ህዝባችን እናሳውቃለን፡፡

LEAVE A REPLY