4ኛ ወንጀል ችሎት በ24 አመቷ ወጣት ንግስት ይርጋ መዝገብ ላይ ብይን ሰጠ

4ኛ ወንጀል ችሎት በ24 አመቷ ወጣት ንግስት ይርጋ መዝገብ ላይ ብይን ሰጠ

 /ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ዛሬ ሰጠ።

የ24 ዓመቷን ንግስት ይርጋን ጨምሮ አምስት ተከሳሾችን የያዘው ይህ መዝገብ የጸረ- ሽብር አዋጁን 652/2009 አንቀጽ 3/4/6 ስር ይከላከሉ የሚል ብይን ሰጥቷል።

በእነ ንግስት ይርጋ ላይ የህወሓቱ አቃቤ ህግ የከፈተው ክስ “የግንቦት ሰባት አባል በመሆን በሽብር ተግባር መሳተፍ” የሚል የፈጠራ ክስ ቢሆንም ስድስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እቢተኝነት በመሳተፋቸውና “የአማራ ህብዝ አሸባሪ አይደለም” የሚል የሚጮህ ድምጽ በማሰማታቸው መሆኑ የሚታመን ነው። የመከላከያ ምስክር ለማሰማትም ለታህሳስ 12 እና 13/2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል።

1ኛ ተከሳሽ የሆነችው ወጣት ንግስት ይርጋ በእስር ላይ የምትገኝበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደራዊና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመባት እንደሆነ ቀደም ሲል ለፍርድ ቤቱ ገልጻለች።

ፍርድ ቤቱም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተከሳሹዋ የቀረበውን ቅሬታ እንዲቀርፍ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበር ቢሆንም፣ ማረሚያ ቤቱ ትዕዛዙን አለማክበሩን ወጣት ንግስት ይርጋ በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ትገኛለች። 4ኛ ተከሳሽ ወጣት አወቀ ገበየሁም ማዕከላዊ በነበረበት ወቅትና አሁንም በቂሊንጦ እስር ቤት በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ የአካል ጉዳት እንደደረሰበት ከዚህ ቀደም ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY