አሁን አሁን የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ጉዳይ ላይ ያላቸዉን የዉክልና ስልጣን አስመልከቶ አዲስ የክርክር ምዕራፍ እየተነሳ ይመስላል፡፡ እስካሁን ይህ ጉዳይ አነጋጋሪ ሳይሆን ቢቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚታዩ ጉዳዮች በተለይም ከሽብረተኝነት ክስ ጋር በተገናኘ ጉዳዩ ተደገጋግሞ እየተነሳ ይገኛል፡፡ ከተነሱ ጉዳዮች ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ከተወሰኑት ዉስጥ፡-
1ኛ. የወልቃይት ሕዝብ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ድርጊቱን ፈፀምን የተባለዉ በአማራ ክልል ዉስጥ ስለሆነ በክልሉ በሚገኙ ፍርድ ቤት ጉዳያችን ሊታይ ይገባል በማለት መቃወሚያ አቅርበዉ መቃወሚያቸዉ ዉድቅ ተደርጓል፡፡
– –
2ኛ. የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ጨምሮ 22 ተከሳሾች የተከሰስንበት ወንጀል ተፈፀመ የተባለዉ በኦሮሚያ ክልል በመሆኑ ጉዳያችን ሊታይ የሚገባዉ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነዉ በማለት የፍርድ ቤቱ ስልጣን ላይ መቃወሚያ አንስተዉ ነበር፡፡ ችሎቱም ሃምሌ 19-2008 ዓ.ም በሰጠዉ ብይን የፀረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 31 የሽብር ክሶችን የማየት ስልጣን የፌደራል ፍርድ ቤት መሆኑን በመጥቀስ መቃወሚያቸዉን ዉድቅ አድርጎታል፡፡
– –
3ኛ. በተመሳሳይ በእነ ብርሃኑ ሙሉ እና ነጋ የኔዉ መዝገብ ክስ የቀረበባቸዉ ተከሳሾች ወንጀሉን ፈፀምን የተባለዉ በአማራ ክልል በመሆኑ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 99 እና 100 መሰረት ክሱ ሊታይ የሚገባዉ ድርጊቱ ተፈጸመበት በተባለ ቦታ ሊሆን ይገባል የሚል መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፍርድ ቤቶች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህጉ ስልጣን የተሰጣቸዉ አገሪቱ በአሃዳዊ ሥርዓት ሥር በነበረችበት ጊዜ ስለሆነ አሁን ላለዉ ፌደራላዊ ሥርዓት ተፈጻሚነት የለዉም፤ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 78 በፌደራል ጉዳይ ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቶ የነበረዉ የዉክልና ስልጣን የሚቆየዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን በክልሎች እስኪያቋቁም በመሆኑና በአዋጅ ቁጥር 322/95 መሰረት በአፋር፣ደቡብ ሕዝቦች፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች ስለተቋቋሙ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የዉክልና ስልጣኑን ስላጣ የተከሳሾች መቃወሚያ ተቀባይነት የለዉም በማለት ጥቅምት 23-2010 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በአብላጫ ወስኗል፡፡
– –
እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ዉሳኔዎች በሕግ ባለሙያዎች መካከል አወያይ መሆን ጀምረዋል፡፡ ጉዳዩን ከቀረበበት አዉድ መመልከቱ አስፈላጊ ቢሆንም ሕጉና መርሁ ምን እንደሚል ከስሩ በመመልከት እኛም የድርሻችን እንበል፡፡
–
#የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ጉዳይ ያላቸዉ ስልጣን የሕግ ማዕቀፍ
– –
ፍርድ ቤቶች በሕግ ያላቸዉ የመዳኘት ስልጣን አንድም ከሕገ መንግስት ወይም ሕግ አዉጭዉ በሚያወጣቸዉ ሕጎች ሊወሰን ይችላል፡፡ በአገራችን የፌደራሉ ሆነ የክልሉ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 78(2) እዉቅና ተሰጥቷቸዉ የተቋቋሙ ናቸዉ፡፡ የክልል ፍርድ ቤቶችም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስካልተቋቋመ ድረስ የፌደራል ጉዳዮች ስልጣን በግልፅ እንደተሰጣቸዉ በግልፅ ተቀምጧል፡፡
– – –
#የፌደራል ፍርድ ቤቶች በክልሎች ለምን ይቋቋማሉ?
– –
የፌደራል ሥርዓት የሚከተሉ አብዛኞቹ አገሮች የፌደራልና የክልል ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም የሁለትዮሽ የፍርድ ቤት አወቃቀር ስርዓት ይከተላሉ፡፡ በክልሎችም የፌደራልን ጉዳይ የሚመለከቱ ፍርድ ቤቶች የሚመሰረቱበትን ስርዓት አብረዉ ይዘረጋሉ፡፡ ጥያቄዉ የሚሆነዉ በክልሎች ለምን የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋም አስፈለገ የሚለዉ ነዉ፡፡
በመስኩ ያጠኑ ልሒቃኖች የፌደራሉን ፍርድ ቤት በክልል እንዲያቋቋም የሚያደርገዉ ትልቁ ገፊ ምክንያት ስጋት ነዉ ይላሉ፡፡ ትልቁ ስጋትም ክልሎች የፌደራሉን ጉዳይ ወይም ፖሊሲ እንደራሳቸዉ አድርገዉ ላያስፈጽሙት ይችላሉ የሚለዉ እንደሆነ ይገልጹና፤ ይሄ ጥርጣሬ ደግሞ የክልል ፍርድ ቤቶች አቅም ላይ ሙሉ እምነት ካለመኖርም ይመነጫል ይላሉ፡፡ በተጨማሪም የፌደራሉን ህግ ከክልል ክልል በተለያዬ ሁኔታ ሊተረጎም ስለሚችል ወጥነት ያለዉ የሕግ አተረጓጎም እንዳይኖር ሊያደርግ ስለሚችል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በክልል መቋቋማቸዉ አጠያያቂ እንዳልሆነ ይገልፃሉ፡፡
– –
የፌደራል ፍርድ ቤቱን ከማደረጃት ዉክልና መስጠት ተመራጭ የሆነዉም በክልሎች የፌደራል ፍርድ ቤት ለማቋቋም ከወጪ እና ከሰዉ ሃይል አንጻርም አስቸጋሪ ስለሚያደርገዉ እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ደረጉ አካሎች ይገልፃሉ፡፡ ለሁሉም ክልሎች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቋቋም ቢባል ተቋሙ ከሚፈልገዉ የሰዉ ሃይል ጀምሮ ሰፊ እና የረጅም ጊዜ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ በዉክልና እያሰሩ ስርዓቱን በሂደት መገንባት የሕግ አዉጭዉ ገፊ ምክንያት እንደሚሆን መገንዘብ ይቻላል፡፡
– –
#የክልል ፍርድ ቤቶች ያላቸዉ የዉክልና ስልጣን አይነኬነት!
– –
የሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 78(2) አማርኛዉ ድንጋጌ በግልፅ እንዳስቀመጠዉ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በክልል እስካልተቋቋሙ ድረስ በፌደራል ጉዳይ የክልል ፍርድ ቤቶች ስልጣን እንዳላቸዉ ነዉ፡፡ የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ጉዳይ ያላቸዉን ስልጣን የሚያጡት በክልሉ ፌደራል ፍርድ ቤት ሲቋቋም ብቻ ነዉ፡፡ በዚህ ድንጋጌ መርሁ የፌደራል ጉዳይ በክልል ፍርድ ቤቶች በዉክልና እንደሚታይ ሲሆን በልዩ ሁኔታ አስፈላጊ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ የክልል ፍርድ ቤቶች የፀና ስልጣን የሚኖራቸዉ ይሆናል፡፡ አሁን በቅርብ እየታዬ ባለዉ ሁኔታ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ጉዳይ በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸዉን የመዳኘት ስልጣን እየተቀበሉት አይመስልም፡፡
– –
ለክልል ፍርድ ቤቶች ዉክልናዉን የሰጠዉ ሕገ መንግስት እንጅ የፌደራሉ ፍርድ ቤት አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት የፌደራሉ ፍርድ ቤት የእኔን ጉዳይ ለማየት የተወከልክና በፈለግሁት ጊዜ ጉዳዬን ማየት እችላለሁ ለማለት የሕግ መሰረት የለዉም፡፡ ምክንያቱም ይህ ዉክልና ተራ ከዉል የሚመጣ ዉክልና ሳይሆን ከሕግ የሚመነጭ ዉክልና ነዉ፡፡ በሕግ የተሰጠ ዉክልና ደግሞ ሊነሳ የሚገባዉ አንድም ሕጉን በማሻሻል አልያም በሕጉ የተቀመጠዉ ሁኔታ ሲሟላ ነዉ፡፡ ክልሎች በፌደራል ጉዳይ ያላቸዉን ስልጣንም በፌደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ሊነጠቁ አይችሉም፡፡ ስልጣናቸዉ ሊወሰድባቸዉ የሚችለዉ ወይ የዉክልና ስልጣን የሰጣቸዉን የሕገ መንግስት ድንጋጌ በማሻሻል ወይም በሕገ መንግስት የተቀመጠዉን ሁኔታ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በክልሎች ሲቋቋሙ ብቻ ነዉ፡፡ እስካሁን ባለዉ ሁኔታም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደረጃ አዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቋቋመላቸዉ አፋር፣ቤንሻንጉል፣ጋምቤላ፣ሶማሌ እና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ብቻ ናቸዉ፡፡ በሌሎቹ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባልተቋቋመባቸዉ የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ሐረሪና ትግራይ ክልል የፌደራል ጉዳዮች የክልል የፍርድ ቤቶች እስካሁን የፀና ስልጣን እንዳላቸዉ ነዉ፡፡ በአምስቱ ክልሎች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቋቋምም ከሕግ መርህ ሆነ ከምክንያታዊ መመዘኛ አንጻር ሌሎች ክልሎች ያላቸዉን ስልጣን ሊያሳጣ የሚችል አይደለም፡፡
– –
#የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርኣት ህጉ ተፈጻሚነት ወሰን፡-
– –
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሕገ መንግስቱ የተሰጠዉን የዉክልና ስልጣኑ ተነስቷል በማለት ሲወስን የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 99 እና 100 አሁን ባለዉ የፌደራል ስርዓት የፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለመወሰን ስልጣን እንደሌለዉ ጠቅሷል፡፡ ይህ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓትህ ሕግ አገሪቱ አሃዳዊ የመንግስት ሥርዓት ስር ትዳደር በነበረበት ወቅት የወጣ ሕግ ቢሆንም አሁንም ሁሉም የወንጀል ክርክሮች የሚመሩበት ስነ-ስርዓት ሕግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ የወንጀል ክስ የሚታይበትን ፍርድ ቤት የሚወስነዉ የሕግ ክፍልም አሁን ባለዉ ሁኔታ እየተሰራበት ያለ ሲሆን ካለዉ የፌደራል ሥርዓት ጋርም የሚጋጭ ነገር የለዉም፡፡ ወንጀል በተፈፀመበት ቦታ ክስ መታየቱም ከየትኛዉም ሕግ ጋር የሚጋጭ አይደለም፡፡ ክልሎች የፌደራልን ጉዳይ እየተመለከቱ የሚገኙት በሕገ-መንግስት ድንጋጌ ተሰጣቸዉ ስልጣን እንጅ በዚህ የስነ-ስርዓት ሕግ አይደለም፡፡ ክልሎች በፌደራል ጉዳዮች ላይ ያልተሻረ እስካሁን የፀና የማየት መብት እስካላቸዉ ድረስ የስነ-ስርዓት ሕጉ ስጋት አይሆንም፡፡
– – –
በአንድ<span lang=”AMH” style=”font