ዶክተር ታደሰ ብሩ በነፃ ተሰናበቱ

ዶክተር ታደሰ ብሩ በነፃ ተሰናበቱ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ የአመራር አባል ይእህኦንኡትን ዶ/ር ታደሰ ብሩን የእንግሊዝ መንግስት በሽብር ጠርጥሮ ከፍቶባቸው ከነበረው ክስ በነጻ አሰናበታቸው።

ከተጠቀሱባቸው ስምንት ክሶች መካከል በኤርትራ ከሚገኝ ታጣቂ ቡድን የስልጠና ቦታ መገኘት፣ በኢንተርኔት አማካኝነት ለሽብርተኝነት ሊጠቅሙ የሚችሉ ጹሁፎችን በማውረድና ሌሎች ክሶች ተከፍቶባቸው ሲከራከሩ ከቆዩ በሗላ በነጻ ተሰናብተዋል።

ክሱን ሲመለከት የቆየው የለንደን ፍርድ ቤት ዶክተሩ የወሰዱት ስልጠና ከሽብር ተግባር ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር እንደሌለው በማጣራቱና ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ፣ ፍትህንና እኩልነትን ለማምጣት የሚታገሉ ሆነው እንዳገኛቸው በመግለፅ ዛሬ በነፃ እንዳሰናበታቸው የዶክተሩ ጠበቃ ገልጸዋል ።

ይህም የኢትዮጵያ አገዛዝ ቡድን የሀገሪቱን ከፍተኛ መዋለ-ንዋይ በማፍሰስ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች ላይ የሳይቨር ስለላ እንደሚያደርግ የሚታወቅ ሲሆን የዶክተር ታደሰ ብሩ ክስም የህወሓት የደህንነት መስሪያ ቤት ለለንደን ፖሊስ ክስ እንዲከፈትባቸው ውትወታ እንዳደረጉ ይታመናል። ዶክተር ታደሰ ብሩ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራርነት በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲ መምህርም ናቸው።

LEAVE A REPLY