ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ባላት ልዩ ጥቅም ላይ ሊካሄድ የነበረው ውይይት አወዛገበ

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ባላት ልዩ ጥቅም ላይ ሊካሄድ የነበረው ውይይት አወዛገበ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ባላት ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሊያደርገው የነበረውን ሕዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ፡፡ውይይቱ ከተጀመረ በኋላ ተቋርጦ ለሌላ ጊዜ የተላለፈው በውይይቱ የተገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና የክልሉ አመራሮች፣ የክልሉ ሰላም ባልተረጋጋበት ሁኔታ በልዩ ጥቅም ጉዳይ ላይ ተረጋግተን መወያየት አንችልም በማለት ባነሱት ተቀቃውሞ ምክንያት መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያለትን ልዩ ጥቅም የተጠራውን ህዝባዊ ውይይት የኦሮሞ ህዝብ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ እንዲጠይቅ ትናንት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ጥሪ አቅርበው ነበር።

አቶ አዲሱ “አከራካሪ በሆነውረቂቅ ህግ ላይ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ህዝብ ተረጋግቶ ሊወያይ አይችልም” በማለት ገልጸዋል።ህወሓት ከብአዴንና ኦህዴድ ጠንካራ ተቃውሞ ስለገጠመው “አዲስ አበባ”ን እንደ ሚዛን ማስጠበቂያ አጀንዳ ሊጠቀምበት እንደፈለገ መረጃዎች እየወጡ ነው።

LEAVE A REPLY