/በፍቃዱ ዘ ኃይሉ/
☞ አድነው ተሾመ (ዛሬ ታኅሳስ 16/2010 ለ4ኛው ችሎት የተናገረ)
☞ ፻ ዐለቃ ጌታቸው መኮንን (አሁን በነጻ የተፈቱ ፤ ለፍርድ ቤቱ ሱሪያቸውን አውልቀው ያሳዩ)
☞ አወቀ ሞኝሆዴ (ከመቶ ዐለቃ መኮንን ጋር በነጻ የተለቀቀ)
☞ አስቻለው ደሴ (ለፍርድ ቤቱ ሱሪያቸውን አውልቀው ያሳዩ)
☞ ፈረደ ክንድሻቶ (ሱሪ ማድረግ ስለማይችል በሽርጥ የሚንቀሳቀስ)
☞ አበበ ካሴ (እግሩን የሚሸመቅቀው፤ እስካሁን ሕክምና ያላገኘ)
ድብደባ ደርሶባቸው ወይም በቂ ሕክምና ሳያገኙ በእስር ላይ እያሉ ከሞቱ የፖለቲካ እስረኞች መካከል በጥቂቱ፣
☞ ተስፋሁን ጨመዳ (ነሐሴ 2004 በቃሊቲ ወኅኒ ቤት እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ ኒሞና ጥላሁን (ሐምሌ 2006 በቃሊቲ ወኅኒ እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ ሙባረክ ይመር (ጥር 2007፣ ቂሊንጦ ውስጥ እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ አየለ በየነ (ሐምሌ 2009፣ ቂሊንጦ ወኅኒ ቤት እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ አብደታ ኦላንሳ (ጥር 2007፣ ቂሊንጦ ወኅኒ ውስጥ እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ አርማዬ ዋቄ ማሞ (ጥቅምት 2010፣ ቂሊንጦ ወኅኒ ቤት እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
☞ መሐመድ ጫኔ (ጥቅምት 2010፣ ቂሊንጦ ወኅኒ እያለ ሕይወቱ ያለፈ)
***
ነገ እስረኞችን ለማሰብ ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ዘመቻ የምናደርገው በሕዝባዊ አገልግሎቶቻቸው ለዚህ ዓይነት ስቃይና ሞት የሚዳረጉ ሰዎች መኖራቸውንም ለማስታወስ ነው።