ቴዲ አፍሮ በኤርትራ መዲና አስመራ የሙዚቃ ዝግጅቶቹን ማቅረብ እንደሚፈልግ አስታወቀ

ቴዲ አፍሮ በኤርትራ መዲና አስመራ የሙዚቃ ዝግጅቶቹን ማቅረብ እንደሚፈልግ አስታወቀ

በአስመራ ሙዚቃዎቹን ማቅረቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ያሻሽላል ብሎ እንደሚያምን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በሰጠው ቃለ ምልልስ ገለጸ።«የሚያስፈልገን የፍቅር፣ ሰላም እና ይቅር ባይነት መንፈስ ነው።

ምክንያቱም አሁን ያሉት ችግሮች የታሪካዊ ቅሬታዎች ውጤት ስለሆኑ ነው። እነዚህን ማራገፍ አለብን። ወደኋላ ልንተዋቸው ይገባል” ሲል ገልጿል።ቴዲ አፍሮ(ቴዎድሮስ ካሳሁን) በኢትዮጵያ ስላለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት አስተያየቱን ሲሰጥ “ልጅ ሆኜ የማስታውሰው እንደ አንድ ሀገር ስንኖር ነው። የምናውቀው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ነው። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንታወቀውና የምንጠራው በብሔር ማንነታችን ነው። ይህ አካሄድም ለሀገራችን እጅግ አደገኛ ነው” ሲል ለዜና ወኪሉ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም ባወጣቸው አልቨሞች ውስጥ ኤርትራን የሚመለከቱ ዜማዎችን በማካተት ይታወቃል።በ1997 “ዳህላክ” ና በ2004ዓ.ም “ፍዮሪና” የተሰኙት ዘፈኖቹን መጥቀስ ይቻላል።ቴዲ አፍሮ ለገና በዓል ሙዚቃዎቹን ለአድናቂዎቹ ለማድረስ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እቀባ ያደረገበትን የህወሓት የአገዛዝ ቡድንን ፈቃድ እየተጠባበቀ እንደሚገኝም ገልጿል።

LEAVE A REPLY