የድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከታህሳስ 3 ቀን ጀምሮ ላለፉት 17 ቀናት አገራችን የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ሰፊና ዝርዝር የሁኔታዎች ግምገማ አካሂዷል፡፡ ስራአስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የመታደስ ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁምበአገራችን የሚታዩ የቆዩና ወቅታዊ ችግሮችን ከነዝርዘር መገለጫቸው በመለየት በመንስኤና መፍትሄዎቻቸው ላይ መክሮ የሃሳብ አንድነትና መተማመን ፈጥሯል፡፡ ችግሮቹን በመቅረፍ በእስካሁን ትግላችን የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን አስጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ቁርጠኝነትና ጠንካራ መግባባትን አረጋግጦ ወጥቷል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች
ድርጅታችን ኢህአዴግ አገራችንን በለውጥ ጎዳና መምራት ከጀመረበት ከ1983 ዓ.ምጀምሮ በሁሉም የህይወት መስኮች መሰረታዊና ተስፋ ሰጭ ለውጥ ሲመዘገብ የቆየ ቢሆንም፣ ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ ለውጡን በተጀመረው ስፋትና ግለት ለማስቀጠል የሚደረገውን ጥረት የሚፈታተኑ ችግሮች እየታዩ መምጣታቸውን ይገነዘባል፡፡ አገራችን በአንድ በኩል በተከተልነው መሰረታዊና ትክክለኛ አቅጣጫ በተገኙ መልካም ውጤቶች እጅግ የሚያስጎመዥ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በፈፀምናቸው ስህተቶችና ከእድገታችን ጋር ተያይዘው በተከሰቱ አዳዲስ ለውጦችና ፍላጎቶች ምክንያት ለጊዜውም ቢሆን በአሳሳቢ ወቅታዊ ችግሮች ተወጥራ የቆየችበት ሁኔታ መፈጠሩን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በትኩረት ገምግሟል፡፡
ለሁሉም የአገራችን ህዝቦች ግልፅ እንደሚሆነው ለበርካታ ዘመናት በማሽቆልቆል ሂደት ውስጥ ለማለፍ የተገደደችው አገራችን ለ25 አመታት ቀና ብላ ስትጓዝ ቆይታለች፡፡ ይህምበሁሉም አገር ወዳድ ዜጎች የሚታመንበትና አለምም የመሰከረለት ነው፡፡ የኢኮኖሚ ውድቀትና ማሽቆለቆል ተገትቶ ለሩብ ምእተ አመት የዘለቀው አገራዊ እድገት ኢትዮጵያችን በትንሳኤ ጎዳና መገኘቷን አብስሯል፡፡ ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲያችን የግልና የቡድን መብቶችን በማስከበር የሰላምና የእድገት መሰረት እንደሆነ በእነዚሁ አመታት ተረጋግጧል፡፡ ብዝሃነት የኢትዮጵያችን መሰረትና መገለጫ እንደሆነ በመቀበል ይህንንኑ በአግባቡ ለማስተዳዳር ያደረግነው ጥረት አገራችን ዜጎች ለረጅም አመታት በፍቅርና መከባበር የሚኖሩባት የሰላም አገር እንደሆነች አስመስክሯል፡፡ ይሁንና ይህ የሚያስጎመዥ እውነታ ከቅርብ አመታት ወዲህ በመታየት ላይ ባሉ ጊዜያዊ ችግሮች የተነሳ ለአደጋ እየተጋለጠና ለሁሉም ማህበረሰቦቻችን የስጋት ምንጭ መሆን በጀመረ አዲስ ክስተት መልክ የሚገለፅበት አዝማሚያ ሰፋ ብሎ ታይቷል፡፡ ከዚህ የተነሳም መላ የአገራችን ህዝቦችኢትዮጵያችንን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች በማውጣት በትግላችን የተመዘገቡ ስኬኮችን ለመጠበቅና ለማስፋት፤ ድክመቶችንና አደጋዎችን ደግሞ በቁርጠኝነት ለማስተካከል የሚሹበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ መንግስትና የለውጡን ሂደት የሚመራው ድርጅታችንም ለዚህ የህዝብ ጥያቄ አስተማማኝ ምላሽ የሚሰጡበት ሁኔታ እንዲፈጠር አጥብቀው ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
የኢህአዴግ ስራአስፈፃሚኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በላይ ጊዜ ያካሄደው ግምገማ በዚህ የህዝባችን ልባዊ ፍላጎትና ቅን አገራዊ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ለዚሁም መላው ድርጅታዊ አቅሙን ተገዥ ለማድረግ በሚያስችል ቁርጠኝነት የተካሄደ ነው፡፡ በመሆኑም ስብሰባው በትናንተናው እለት በመላው የአገራችን ህዝቦች ከባድ ተጋድሎ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለመጠበቅና ለማስፋት እንዲሁም ከምንም ነገር በላይ በአመራር ድክመት የተፈጠሩትን አደጋዎችና ስጋቶች ለመቅረፍ በሚያስችል ስምምነትና መግባባት ተጠናቋል፡፡
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፉት አስራ ሰባት ቀናት ባደረገው ግምገማ በየደረጃው ባሉ የአመራር እርከኖች በተለይ ደግሞ በከፍተኛው አመራር ደረጃ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ እጦት ስር እየሰደደ እንደመጣ አረጋግጧል፡፡ ይህም ሐሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርባቸውን የመታገያ መድረኮች የሚገድብና የሚያጠብ ስለዚም ደግሞ በአመራሩ ውስጥ የአመለካከትና የተግባር አንድነትና ጥራት እንዳይፈጠር መሰናክል ሆኖ እንደቆየ ተመክልቷል፡፡ ይህ ችግር በዋነኛነት በድርጅታችን ከፍተኛ አመራር ደረጃ ከታየው የተዛባ የስልጣን አተያይና አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የተከተሰተ ሲሆን ችግሩ የድርጅታችን አይነተኛ መለያ የሆነውን ዴሞክራስያዊነት በማዳካም ሳይወሰን ስልጣን የህዝብ መገልገያ እንዲሆን የጀመርነውን መልካም ጉዞ ለአደጋ ያጋለጠ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ዴሞክራሲ እየጠበበ አድርባይነት በመስፋፋቱ ምክንያት በግልጽነትና በመርህ ላይ ተመስርቶ ከመተጋገል ይልቅ መርህ አልባ ግንኙትና አካሄድ ማስፈን የተለመደ ስልት ወደመሆን ተሸጋግሯል፡፡ ይህን የመሰለው በጠባብ ቡድናዊ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ መርህ አልባ ግንኙነት ኢህአዴግና አባል ድርጀቶቹን የማዳከም ውጤት አስከትሏል፡፡ ልማታዊ መንግስትታት በጠንካራ ዲስፒሊንና የሃሳብና የተግባር አንድነት የሚታወቁ ሆኖ እያለ ተገቢ ባልሆኑ ጥቅሞች ላይ የተመሰረቱት የቡድን ትስስሮች ልማታዊ መንግስታችንና ድርጅታችን ተልእኮአዋቸውን በብቃት እንዳይፈፅሙ ከፍተኛ መሰናክል ሆኖ እንደቆየ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አረጋግጦአል፡፡
በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴያችን ግምገማ መሰረት ማንኛውም መርህ አልባ ቡድናዊ ትስሰር ከምንም ነገር በፊትና በላይ እያንዳንዱን ብሄራዊ ድርጅትና በእሱም የሚራውን ህዝብ የሚጎዳ አደገኛ ጉደይ ነው፡፡ በመቀጠልም በግባራችን የሚመራውን የጋራ ትግልና አገራዊ የለውጥ ሂደቱን ለአደጋ የሚያገልጥ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ስራአስፈፃሚ ኮሚቴው በየትኛውም ክልል ሆነ ብሄራዋ ድርጅት የሚከሰቱ መርህ አልባ ጉድኝቶች በጥልቅ እየተፈተሹ ሊወገዱ እንደሚገባ ወስኗል፡፡
እንደሚታወቀው በአገራችን የሚገነባው ፌዴራላዊ ስርዓት መላ የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ለዘመናት ያካሄዱት ትግል ውጤት ነው፡፡ አዲሲቱ ኢትዮጵያ ከየትኛውም ህብረብሄራዊ አገር የምትለየው በዝሃነትን በማወቅና በማክበር ነው፡፡ ለ25 አመታት የተገነባው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የቋንቋ፣ የባህል፣ የታሪክ እኩልንተን አረጋግጦአለ፡፡ የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ካልሆነ በቀር በሌላ የማይተዳደሩበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ በፊዴራላዊ አስተዳደራዊ ስርአታትን በእኩልነትና በመተሳሰብ የሚሳተፉበትን ሁኔታም አመቻችቷል፡፡ በዚህ የተነሳ ስርዓቱ ለበላይነትና የበታችነት የማይመች ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ በተግባርም እኩልነት እንጂ የባላይነትም ሆነ የበታችነት የማይፈጠርበት ስርዓት ተገንብቷል፡፡ ይህንን መሰረታዊ መርሆ የሚነካ ማንኛውም ዝንባሌ የበላይነትን በዘላቂነት ሊፈጥር የማይችልና ከመኖቆር ውጭ ሌላ ውጤት የማያስገኝ እንደሚሆንም ይታመናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ለሩብ ምእተ አመት በእኩልነትና በሰላም የዘለቀው ስርዓታችን የዚህ ውጤት እንደሆነ ስራ አስፈፃሚያችን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ሽፋን ይህንን የእኩልነት ስርዓት ለማዳከም የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት እንደሌለውና ሊመከት እንደሚገባው ወስኗል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ወይም በሌላ ብሔር ህዝብና ድርጅት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ጥገኛ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን እንቅስቀሴ ማክሰም እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶች በሚያስተዳድሩት ክልል ውስጥ ያሉ ጥገኞችን ያለልዩነትና ማመንታት መታገል እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ሥራ አስፈፃሚው በድርጅታችን የዴሞክራሲ መጥበብ እዛው በዛው የውሳኔዎችን በታማንኝነትና በቁርጠኝነት የመፈፀም ዲሲፒሊንን እያላላ እንደመጣ አረጋግጦአል፡፡ በዚህ የተነሳ በድርጅትና በመንግስት ቋሚ መመሪያዎች በመገዛት መፈፀም የነበረባቸው ተግባራትና መሰጠት የነበረባቸው የእለት ተለት ውሳኔዎች እየቀሩ በብዙ የመንግስት መ/ቤቶች ህዝብ የሚጠብቃቸው አገልግሎቶች የማይሟሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
በአጠቃላይ በድርጅታችን በተለይም ደግሞ በሥራ አስፈፃሚው ውስጥ የታየው የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር አደጋው በድርጅቱ ውስጥ ብቻ ታጥሮ የቀረ አልነበረም፡፡ የህዝብ መብትን በማክበርና ተገቢውን ህጋዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታን ባለመወጣት ጭምር የሚገለፅ ነበር፡፡ ከዚያም አልፎ ዴሞክራሲያችንን ማስፋትና ማጠናከር ሲገባ በተለያዩ መንገዶች የማጥበብ አዝማሚያም ተስተውሏል፡፡ ህገ መንግስታዊ ስርአታችን ልዩ ልዩ ጥቅሞችና ፍላጎቶች እንዲሁም በእነዚህ ላይ የተመሰረቱ ልዩነቶች በዴሞክራሲያዊ፣ ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲስተናገዱ በቂና አስተማማኝ እድል ከፍቶ እያለ አመራራችን ዴሞክራሲውን የማስፋት ግዴታውን ባለመወጣቱ ችግሮችና ልዩነቶች በግጭት መንገድ የሚፈቱበት ሁነታ እንዲፈጠር አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ይህም ለሰላማችን መታወክ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
ለመላው የአገራችን ህዝቦች ግልፅ እንደሚሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርከት ባሉ የአገራችን አካባቢዎች ሰላመና መረጋግት እየደፈረሰ ሁከት የለት ተለት ከሰተት እየሆነ መጥቷል፡፡ በክልሎችም ሆነ በክልሎች መካከል በልዩ ልዩ ሰበቦች የሚከተሰተው የሰላም መደፍረስ ለዜጎቻችን አሳዛኝ ሞት መበራከትና መቁሰል እንዲሁም ከባድ መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ የንብረት ውድመትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መገታት አስከትሏል፡፡ ይህ ለረጅም አመታት በሰላም በኖረችው አገር ውስጥ የስጋት መንፈስና ጭንቀት ፈጥሯል፡፡ ከበየቦታው እየተነሱ ያሉ ግጭቶች ከሰው ሞትና ከንብረት ውድመት በዘለለ የሃገራዊ ሕልውናችን ለአደጋና ሕዝባችንን ለጥፋት ቋፍ ያደረሱበት ሁኔታ ከመኖሩ በላይ ለውጭ ጥቃት ተጋላጭነታችንን የመጨመር ውጤት አስከትለዋል፡፡ ይህም በአጭር ቃል የመበልፀግ ተስፋና የሐገራዊ ሰላም መናጋት የተፋጠጡበት ሁኔታ ላይ እንደድንገኝ አድርጎናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ስራአስፈፃሚ ኮሚቴያችን ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲያችንን በታማኝነት ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መድረኩ የሚጠይቀውን ሁኔታ መነሻ በማድረግም ማስፋትና የግጭት መንስኤዎችን መቅረፍና የአገራችንን ሰላም ወደተለመደው አስተማማኝ ሁኔታ በአጭር ጊዜ መመለስ እንደሚገባ ወስኗል፡፡
በአገራችን የሚገነባው ህገመንግስትታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍላትና ጥቅሞች ብዝሃነት ላይ የተመሰረት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በድርጅታችንና በመንግስት መሪነት ለ25 አመታት የቀጠለ ቢሆንም ከቅርብ አመታት ወዲህ የአስተሳሰብ ብዝሃነት በአግባቡ እንዲገለፅ የሚያደርግ ተጨባጭ ሁኔታ እየተዳከመ መጥቷል፡፡ ይህንን ችግር በጊዜና በአግባቡ ተገንዝቦ ማስተካከል የሚገባው ድርጅታችን ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ረገድ ያሳየው ዳተኝነት የመድብለ ፓርቱ ስርግቱን ችግር እንዲገጥመዉ አድርጓል፡፡ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት ጉዳይ ምንም እንኳ በአዋጅና በድርጅታችን በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የሚመሰረት ባይሆንም በዚህ ረገድ ልንወስደው ይገባን
የነበረውን ርምጃ ከመውሰድ አንፃር ሰፊ ክፍተት እንደነበር ሥራ አስፈፃሚው ይገነዘባል፡፡
ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሁነኛ ድርሻ ካላቸው ተቋማት መካከል የሃገራችን ሚዲያና ፕሬስ በሚገባው ደረጃ ነፃነታቸው ተጠብቆ የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው ያገለግሉ ዘንድ የተደረገው እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በግምገማው ተመልክቷል፡፡ በዚህ ረገድ የታየው ዘገምተኛ ዕድገት እንደተጠበቀ ሆኖ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልልም ይሁን በፌዴራል ያሉ የህዝብ የሚዲያ አውታሮች ሕግና ሥርዓትን ጠብቀው የማይሠሩበት ሁኔታ እያመዘነ የህዝቡን ሰላምና አብሮ የመኖር ገንቢ ባህል የሚሸረሽሩ ሰበካዎች የሚሰጥባቸው፣ ብሎም ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ አጥፊ ቅስቀሳዎች የሚካሄድባቸው እየሆኑ ለመምጣታቸው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚም ሆነ የሚመራው መንግሥት ድክመት አስተዋፅኦ እንዳደረገ ይቀበላል፡፡
አመራሩ ዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ በመገንባትና በህገመንግስታዊ ስርዓታችን ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር እየተገባው የህዝብ የተደራጀ ሲቪል እንቅስቃሴ እንዳልተጠናከረ አረጋግጧል፡፡ በአገራችን ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ዋስትና የሚኖረው ከአዋጅ አልፎ ህዝብ በተደራጀና ንቁ አኳኋን ሲሳተፍና ሲጠቀምበት ቢሆንም በዚህ ረገድ የተደረገው እንቅስቃሴ የሲቪል ማህበረሰቡን ተሳትፎ መሆን በሚገባው ደረጀ ከፍ ለማድረግ ያስቻለ እንዳልሆነ ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሰረት በአገራችን የሚገነባው ዴሞከራሲያዊ ስርአት የሚታይበትን የሲቪል ማህበረብ ተሳትፎና ሁለገብ እንቅስቃሴ ገደብ ከጣሉበት ችግሮች በማላቀቅ ማጠናከር እንደሚባ ታምኖበታል፡፡ አመራሩ የዴሞክራቲክ ተቋማት ግንባታና የህዝብ የተደራጀ ተሳትፎ የሞት የሽረት ጉዳይ እንደሆነ ተገንዘቦ ባለመንቀሳቀሱ የተፈጠረውን መሰረታዊ ጉድለት ለመፍታት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ልክ እንደዴሞክራሱው ሁሉ በአገራችን የህልውና ጥያቄ የሆነውን መልካም አስተዳደርን የማስፈን እንቅስቃሴያችን በአመራር ድክመት ምከነያት ለበረካታ ችግሮች እንደተጋለጠ ስራ አስፈፃሚኮማቴው አረጋግጧል፡፡ በዚህ ረገድ የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማስፋት፣ የህግ የበላይነትን ለማደረጋገጥ፣ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራርን ለማንገስና ውጤታማና ቀልጣፋ አስተዳዳር ለመገንባት የተደረጉ ጠረቶች ያስገኙትንን መልካም ፍሬ መጠበቅና ማስፋት አዳጋች ሆኖ ቆይቷል፡፡ በየደረጃው የመኑ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት በቅን ልቦናና መንግስታዊ መመሪያዎችን በተከተለ አኳኋን ህዝቡን የሚያገለግሉና ተሳትፎና ተጠከሚነቱን የሚያረጋግጡበት እድል ቀንሷል፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የህዝብ ምሬት ተፈጥሯል፡፡ ስራ አስፈፃሚው ይህ ችግር ከምንም ነገር በላይ በከፍተኛው አመራር ደረጃ በሚታይ ጉድለት ምክንያት የተፈጠረና የተባበሰ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡ የህግ የበላይነት የማስፈን ድክመት በመታየቱ በሙስናም ሆነ በሌሎች ጥፋቶች ውስጥ የተዘፈቁ ግለሰቦችን በወቅቱና ህጋዊና አስተማሪ በሆነ መንገድ መጠየቅ ሳየቻል ቆየቷል፡፡ ዜገች በህገመንግስቱ ዋስትና ያገኙ መብቶቻቸው የሚጥሱ ሰዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ መሆን በሚገባው ደረጃ ሳይፈፀም ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም መንግስት የህዝብና የአገር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በነደፋቸው ፕሮጄክቶት ዙሪያ የሚታዩ የአፈፅፀምና የስነምግባር ችግሮችን አስተማማኝና ውጤታማ በሆነ መንገድ የማረምና የማስተካከል ጉድለት ታይቷል፡፡ በዚህ የተነሳ አገራችንን በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ሊያሰፉ የሚችሉ ፕሮጄክቶች፣ የጊዜ የዋጋ ንረትና የሃብት ብክነት የሚታይባቸው ሆነዋል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እነዚህ የመልካም አስተዳዳር ችግሮች ህዝብና አገርን ያልተገባ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንደሆኑ በመገንዘብ በአፋጣኝ እንደስተካከሉ ማድረግ እንደሚገባ አምኖበታል፡፡ በዚህ ረገድ ይህንን የመልካም አስተዳደር ችግር በተግባር ማቃለል ሲገባ ባጉል ተስፋና በባዶ ቃልኪዳን የመሸንገል ህዝበኛ አዝማሚያዎች በጥብቅ መመከት እንዳለባቸው ወስኗል፡፡
ድርጅታችን የሁሉም ህዝቦች እኩልነት በተከበረባት አገራችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባትን መርህ ተክትሎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በተጨባጭም አገራችንን ከመበታተንቋፍ አውጥቶ አዲስ አይነት ዴሞክራሲያዊ አንድነትና የእኩልነት ትስስር በመገንባት ረጅም ርቀት ተጉዟል፡፡ ይህ በአገር አቋራጭ የመሰረተ ልማት አውታሮች የማይበጠስ ትስስር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሃገራችን በየደረጃው እየተካሄዱ ያሉና ሊካሄዱም የሚገባቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች የድርጅታችን ሃገራዊ ራዕይና የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችንን በሚያጠናክር መልክ በማስኬድ ረገድ ቁጥራቸው የማይናቅ ጉድለቶች በአመራሩ ተፈጽመዋል፡፡ በአጭሩ በህብረተሰባችን ዘንድ ህገመንግሥታዊ ሥርዓቱን፣ ልማታዊ አስተሳሰብና፣ በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ኢትዮጵያዊ አንድነት በማጠናከር ረገድ የተሰራው ስራ መሆን የሚችለውን ያህል ውጤት ሳያመጣ እንደቀረ ሥራ አስፈፃሚው ባደረገው ግምገማ ማረጋገጥ ችሏል፡፡ በዚህ የተነሳ ብሄረሰባዊና አገራዊ ማንነትን አስተሳስሮ በመገንባት በኩል የታየውን ጉድለት በአፋጣኝና በአስተማማኝ መንገድ መፍታት እንደሚኖርብን ታምኖበታል፡፡
ከላይ የተገለፁት ችግሮችና በተራዘመ ትግል የተገነባችውን አገር ለአደጋ ማጋለጥ የጀመሩት ጉድለቶች በዋነኛነት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር በተለይም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ድክመቶች ናቸው፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱና የድርጅትና የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች በተናጠልና በጋራ፣ ስትራተጅያዊና ታክቲካዊ አመራር የመስጠት ሃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው የተፈጠረ ችግር ነው፡፡ በዚህ ግምገማ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የመንግስት የበላይ አመራሮች ወቅቱ የሚጠይቀውን ስትራቴጂያዊ አመራር የመስጠት ጉድለታቸው ሰፊ እንደሆነ ታይቷል፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ችግር አስቀድሞ የመለየት፣ ተንትኖ የማወቅ፣ የመፍቻ መንገዶች የመተለምና በዚሁ መሠረት የመፍታት ብቃቱ ወቅቱና መድረኩ ከሚጠይቀው ደረጃ ጋር አብሮ ባለማደጉ የተወሳሰበውን አገራዊ መድረክ በብቃት የመምራት ጉድለት እንደነበረበት የጋራ አቋም ተይዟል፡፡ በመሆኑም ለተፈፀመው ስህተትና ለደረሰው ጉዳት ከፍተኛ አመራሩ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ከዚህ በመነሳት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መላ የአገራችን ህዝቦች በከባድ ተጋድሎአቸው ያስመዘገቡዋቸውን ድሎች ጠብቆና አስፍቶ ለማስቀጠል ባለመቻሉ፤ እንዲሁም በድርጅታችን ውስጥም ሆነ በአገራችን ውስጥ የሚታዩ ልዩ ልዩ ችግሮችን በጊዜና በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ ለመፍታት ባለመቻሉ ለደረሰው ጉዳት ሙሉ ሃላፊነቱን ከመውሰድ በተጨማሪ ለመላ የአገራችን ህዝቦችና የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎችን ልባዊ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግ የትግልና የለውጥ ድርጅት ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በማሽቆልቆል ውስጥ የቆየችውን አገር ለሩብ ምእተ አመት በእድገትና የለውጥ ጎዳና እንድትገሰግስ ያደረገውን ጥረትና የተመዘገቡትን ህዝባዊ ድሎች ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረጉም የተሰማውን ከልብ የመነጨ ፀፀት ይገልፃል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዳይደገምም እንዳለፉት አመታት ሁሉ በቁርጠኝትና በፅናት እንደሚንቀሳቀስ ቃል ኪዳኑን ያድሳል፡፡ ለማናቸውም ፈተና ሳይንበረከክ ከድል ላይ ድል በማስመዝገብ የመጓዝ እንቁ ታሪክ ያለው ድርጅታችን ኢህአዴግ አሁን በአገራችን የሚታየውን ሁኔታ እንደሚያስተካከልና የድል ጉዞውን እንደሚያስቀጥልም ቃል ይገባል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከላይ በተገለፀው ግምገማና መግባባት ላይ በመመስረት ከዚህ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ አጣዳፊ ችግሮችን እየፈታ ለዘላቂ ለውጥ መስራት እንዳለበት ወስኗል፡፡
1. ባለፉት 17 ቀናት ባካሄደው ግምገማ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የሕዝባችንን የዴሞክራሲና የልማት እንቅስቃሴ በማጎልበት ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥና ለማስፋት፤ አስተማማኝ ሰላም ባጠረ ጊዜ ማረጋገጥና ሕዝባችን ወደተረጋጋ ኑሮው እንዲመለስ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት የሕዝባችንን ሰላማዊ ኑሮ የሚያውኩ ማንኛውም እንቅስቃሴዎች ከህዝብ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል መንግሥት ሙሉ ሃላፊነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ተወስኗል፡፡ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ላፍታም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደማይገባውና በዚህ ረገድ የሚታዩ የህግ ጥሰቶችን በመቆጣጠር ህግና ሰላምን በአስተማማኝ ደረጃ ማስፈን እንዳለበት ተወስኗል፡፡ በየአካባቢው በሕገወጥ መንገድ የሚደረጉ መንገድ የመዝጋት፣ የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት የማወክ እንዲሁም የሕዝቡን የእለትተለት እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉሉ የቡድንም የተናጠልም እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡ በወሰንም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች