ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በአዲስ አበባ ቃሊቲ በግፍ እስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፔን አዋርድስ 2018(PEN Awards 2018) አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

አስራ ስምንት ዓመት ተፈርዶበት ሰባት ዓመታትን በእስር ቤት ያሳለፈው እስክንድር በእስር ላይ እያለ ከዚህ በፊትም ሌሎች ሁለት አለም አቀፍ ሽልማቶችን አሸንፏል።

እስክንድር ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ የህትመት ሚዲያ ላይ ጉልህ አስተዋፅዖ አበርክቷል።

ጋዜጤኛ እስክንድር ነጋ ሟች ጠቅላይ ሚኒሰቲር መለስ ዜናዊን “ለ21 አመት እርስዎን በአንድ ወንበር ላይ ተቀምጠው ማየት እንደአንድ ዜጋ ሰለቸኝ…” በማለት በጻፈው ጽሁፍ እና ሌሎች ጠንካራ መጣጥፎቹ በአገዛዙ ጥርስ ውስጥ ገብቶ ለእስር የተዳረገ ጋዜጠኛ መሆኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY