በወልቂጤ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል

በወልቂጤ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ ጠዋት ጀምሮ እስከ ሰባት ሰዓት የዘለቀ ግዙፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። በሰልፉ ላይ በከተማ የሚኖሩ ሁሉም ጎሳዎች የተሳተፉበት ሲሆን መንገዶች ተዘግተዋል፣ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴዎችም ሙሉ በሙሉ ተቋርጠው መዋላቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። በሰልፉ ላይ ከተነሱት በርካታ ጥያቄዎች መካከል፦

ሀ. የጉራጌ፣ስልጤ አማራና ኦሮሞ ህብረት አንድ ነው፤

ለ. አማራና ኦሮሞን መግደል ይቁም፤

ሐ. ከአስር ዓመታት በፊት ሆስፒታል ይገነባል ተብሎ የተቀመጠው መሰረተ-ድንጋይ ወደ ትግራይ ክልል በመወሰዱ ይመለስልን የሚሉና ስርዓቱን የሚያወግዙ በርካታ መፈክሮች ሲሰሙ መዋላቸው ታውቋል።

የኢህአዴግ አባል ድርጅት ሊቀ መናብርት ከሁለት ሳምንታት በፊት እስረኞችንና ሌሎች የሀገሪቱን ችግር በመፍታት ሀገሪቱን አረጋጋለሁ፤ ህገ-ወጥ ሰልፎችንም በሀይል አስቆማለሁ ቢልም በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ህዝባዊ አመፆች እየተካሄዱ ነው።

LEAVE A REPLY