/ጌታቸው ሽፈራው/
የወልዲያ ወጣቶች ጥር 12/2010 ዓም የሚካኤልን ታቦት በሚያጅቡበት ወቅት በመንግስት ጦር የተገደሉትን ንፁሃን ቤተሰቦች ለቅሶ እንዳይደርሱ ተከልክለዋል።
ለነገ ጥር 19/2010 ዓም 200 ያህል የወልዲያ ወጣቶች ባነርና ቲሸርቶችን አሰርተው፣ የሚካኤል ታቦትን ሲያጅቡ የተገደሉትን ንፁሃን ቤተሰቦች ዘንድ ለቅሶ ለመድረስ በዝግጅት ላይ እያሉ አስተባባሪዎች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደተደረገባቸው፣ ለቅሶ ቢሄዱ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችሉ እንደተገለፀላቸው ከአስተባባሪዎቹ መካከል አንዱ ገልፆልኛል።
“ለቅሶ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው፣ የተገደሉት ወገኖቻችን ናቸው። መብታችን ነው ብለናቸዋል።ሆኖም ለመሄድ የተመዘገቡትን እያገኙ አስፈራርተዋቸዋል። ለቅሶ እንዳንደርስም ተከልክለናል” ሲል ገልፆአል። ወጣቶቹ በደረሰባቸው ማስፈራሪያና ክልከላ ለቅሶ ለመድረስ ይዘውት የነበረውን ፕሮግራም ላልተወሰነ ጊዜ እንዳራዘሙት ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ዛሬ ጥር 18/2010 ዓም ወልዲያ ከተማ ላይ “በቴዎድሮስ ሀገር አንፈራም፣ ወያኔ ይውደም……” እና መሰል መልዕክት የያዙ ወረቀቶች ተበትነው በመገኘታቸው፣ እንዲሁም የገብርኤል ታቦት የሚወጣበት በመሆኑ ወልዲያ ከተማ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልፆል