/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የዛሬ ሳምንት የጥምቀት ዓመታዊ ባዓል በሚያከብሩበት ወቅት የስርዓቱ ልዩ ጠባቂ በሆኑ የዓጋዚ ወታደሮች ወጣቱን በጅምላ ከጨፈጨፉ ወዲህ በአካባቢው ከፍተኛ አለመረጋጋት ተፈጥሯል።
ትናንትና ከትናንት በስቲያ በቆቦ ከተማ በነበረው ከፍተኛ ተቃውሞ ከ9 ሰዎች በላይ በግፍ ተገድለዋል። ከ300 በላይ ወጣቶች ታፍሰዋል። በቆቦ ከተማ ባዛሬው እለትም ምንም አይነት የህዝብ እንቅስቃሴ እንደማይታይባት ታውቋል።
ዛሬ በጠዋት የተጀመረው የመርሳ ወረዳ ህዝባዊ ተቃውሞም የሰው ህይወት እንዳለፈበት ታውቋል። ወደ ህዝብ ይተኩስ የነበረ አንድ ዳኛ በህዝብ መገደሉ ተነግሯል። የወረዳው ፍርድ ቤትም ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል።
የስርዓቱ ወታደሮችም ተቃውሞውን ለመበተን እንደተለመደው ከፍተኛ ተኩስ እያሰሙ ነው። የስርዓቱ ደጋፊ በሆኑ ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየደረሰ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።