/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌና ሌሎች 746 የፖለቲካ እስረኞች ነገ እንደሚፈቱ ዘገበ።ጋዜጠኛ እስኢክንድር ነጋ፣ እንዷለም አራጌ፣ አበበ ቀስቶና ሌሎች ከመቶ በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞችን “የግንቦት ሰባት አባል ነን” ብላችሁ ፈርሙ በመባላቸውና እስረኞችም “ባልዋልነበት አንፈርምም” በማለታቸው ስጋት ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
በዛሬው እለት እስረኞቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተቀላቀሉ ሲሆን በመጥፎነቱ የሚታወቀው እስር ቤት ቅጥር ግቢ ታሳሪዎቹን ለመቀበል በርካታ ህዝብ ተጥለቅልቆ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህዝቡ ጀግኖቹን በመቀበል ለቤተሰቦቻቸው በክብር ያሰተከበ ከመሆኑም በላይ እስረኞቹን የጫኑ መኪኖችን በማጅብ ‘ውሮ ዎሸባዮ…’ የሚለውን ዜማ ሲያሰማ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
የእስረኞችን መፈታት አስመልክቶ ትላንት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሚከተለው መልኩ ዘግቦታል።
“እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 746 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋረጦ ነገ እንደሚለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ገለጸ።በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጌቱ ጋሩማ፣ አቶ ተስፋዬ ሊበን እና አቶ በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጦ ዛሬ ተለቀዋል።
ታራሚዎቹ እና ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ የተደረገው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ጉዳያቸው ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት እየታየ እንዲለቀቁ በወሰነው መሰረት ነው።ይቅርታ የሚደረግላቸው ሰው በመግደል፣ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ የአገር ኢኮኖሚ ለማውደም በመሳተፍ፣ ህገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ያልተሳተፉ ፍርደኞችና ተከሳሾች እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ መሰረት በፌደራል ደረጃ በሽብር፣ በሁከትና ብጥብጥ፣ በሀይማኖት አክራሪነትና በተለያዩ ወንጀሎች ክሳቸው በሒደት ላይ የሚገኙና የእስር ቅጣት ተላልፎባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 417 ታራሚዎች ነገ ከማረሚያ ቤት ይወጣሉ።በተመሳሳይ ጉዳያቸው በህግ በመታየት ላይ የነበሩ 329 ተጠርጣሪዎችም የተሃድሶ ስልጠናውን ጨርሰው ነገ እንደሚለቀቁ ገልጿል።”