ህወሓት ከሁለት ዓመታት በፊት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር በማፍሰስ “የካቲት 11”ን በጭፈራ ያከብር ነበር።
ዘንድሮ ደግሞ ይችን ትንሽየ መግለጫ በማውጣት አስቦት ይውላል። የሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ታሪክ ሊሆንም ይችላል።
**********
“የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማእከላዊ ኮሚቴ ድርጅቱ የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 43ኛ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ህወሓት እንደ ቀድሞው ሁሉ ህዝባዊ ውግንናውን መልሶ ለመጨበጥ የሚያስችለው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት ላይ ሆነን የምናብረው የየካቲት 11 ወርቃማ ቀን ከሁሉ በላይ የህወሓት አመራር ባሳየው ድክመት የተነሳ በክልሉ ህዝብ ላይ የደረሱ በርካታ ችግሮች እና የእምነት መጓደል ተስተካክሎ ወደ ቀደመ መስመሩ በተሟላ ሁኔታ የሚመለስበትን ሁኔታ ለመፍጠር ቃላችንን የምናድስበት ይሆናል ብሏል፡፡
ህወሓት ለእህትና አጋር ድርጅቶች ባስተላለፈው መልዕክት፤ በድርጅታችንም ሆነ በሀገራችን ላይ ተፈጥሮ ያለው ችግር ሊፈታ የሚችለው በመርህ ላይ በተመሰረተ ትግል ብቻ መሆኑን ገልፆ በመስመራችን ላይ የሚሰነዘረውን የጠላት ዘመቻ በጋራ በመመከት የሀገራችንን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ዛሬም እንደቀመው ሁሉ ከእህትና አጋር ድርጅቶች ጎን መቆሙን አረጋግጧል።
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦችም በአሁኑ ወቅት በሀገራችንና በህዝባችን ላይ አንዣቦ ያለው የጥፋት ደመና እንዲወገድ፤ በኢሕአዴግ ሃያል መስመር እንዲፈታ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልፆ ልማትና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የበለፀገች ኢትዮጵያን የመገንባት ጉዟችንን አጠናክረን እንድንቀጠልም ጥሪውን አቅርባል።”