አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስራ ላይ ሊውል ነው ተባለ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስራ ላይ ሊውል ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የተለያዩ ምንጮች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ለ10 ወራት ተግባራዊ ተደርጎ ለውጥ ማምጣት ያልቻለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተመልሶ ስራ ላይ ሊውል መሆኑን ገለፁ።

ትናንትና ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ የነበረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለሦስት ወይም ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን ምንጮች ገልጸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጁን ለማወጅ የወሰነበት ምክንያት “በአንዳንድ በሀገሪቱ አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩና እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በማሰብ ነው።” ማለቱም ታውቋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ነገ ጠዋት መግለጫ እንደሚሰጡም ታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እረፍት ላይ በመሆኑ ምክንያት በ“ህገ-መንግስቱ” አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሰረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በ15 ቀናት ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ 2/3ኛ ድምፅ ማግኘት እንዳለበት በመደገጉ፤ አዋጁ ለምክር ቤት ሳይቀርብ እስከ 15 ቀናት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰራተኞቹ ከአዲስ አበባ ውጭ ጉዞ እንዳያደርጉ አስጠቅቋል። ዛሬ ጠዋትም አምባሳደር ማይክ ሬይነር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ለውጥ አሜሪካ እንደምትደግፍም አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY