/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በህዝባዊ እምቢተኝነት አመጽ እጁን የኋልዮሽ የተቀፈደደው የህውሃት መራሹ መንግስት ለዘጠኝ አመታት አስሮ ያቆያቸውን የበአዴን የጦር መኮንኖች መልቀቁ ታወቀ፡
የኢህዴን የጦር መሪዎች የነበሩት እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ ኢንጂነር መንግስቱ አበበ፣ ኮለኔል አበረ አሰፋ፣ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ፣ ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢኒስፔክተር አመራር ባያብል፣ ነርስ የሸዋስ ማንገሻ፣ዋና ሳጅን ጎበና በላይ፣ ሳጅን ይበልጣል ብራሃኑ በእስር ከነበሩበት ከዝዋይ ማጎሪያ በአሁኑ ሰዓት ተፈተው ወደ መዲናይቷ አዲስ አበባ ጉዞ መጀመራቸውን ምንጮች የገለጹ ሲሆን ። በአዲስ አበባ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሃገርን በመክዳት ወንጀል ተከሰው እስከ እድሜ ይፍታህ የተፈረደባቸው እነኝህ መኮንኒችና ባለስልጣናት መንግስትን ለመገልበጥ ሲያሴሩና ሲዘጋጁ ተደርሶባቸዋል ተብለው ወደ እስር ቤት መወርወራቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡