ሊያነቡት የሚገባ -የግንቦት 7 ሙሽራው,,,, /አንዋር አንዋር/

ሊያነቡት የሚገባ -የግንቦት 7 ሙሽራው,,,, /አንዋር አንዋር/

ትጉህ ነው እንደዛውም ቅን ሰው አክባሪ ነው፣ የሀገሩ ጉዳይ ከተነሳ ግን ነብር ይሆናል፣ አምባገነኑን ህወሀት/ኢህአዴግ ሲቃወም፣ ጉድሉትን ሲተነትን ይገርማል፣ ሀገሩን ሲወድም ገደብ የለውም፣ ሳኡድ አረቢያ ሄዶ ብዙ ተንከራቶዋል፣ እጅ ሳይሰጥ በራሱ ብርታት እና በጓደኞች እገዛ ጥሩ መስራት ጀምሮ እያለ ሀገር መሄድ እንደሚፈልግ ተናገረ፣ ጓደኞቹ እንዳይሄድ መክረውት ነበር፣ ማንም አልሰማም፣ የሚሄደው ለሰርግ እንደሆነና ለረጅም ጊዜ አስቦት የወሰነው መሆኑን በመናገር ተነስቶ ሄደ፣ በሄደ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ሁሉ ነገር ጨርሶ ሰርጉን አደረገ።

ሆኖም ሰርጉ ባደረገ በሁለተኛው ቀን ተይዞ ማዕከላዊ መግባቱ ተሰማ፣ ወዲያው አይጋ ፎረም የሚባለው የህወሀት ድህረ ገፅ፣ “የግንቦት 7ቱ ሙሽራ በአዲስ አበባ!” በሚል አረእስት ደረጄ ደበበ መያዙንና፣ የመካከለኛው ምስራቅ የግንቦት 7 የከፍተኛ አመራር መሆኑን እንዳመነና፣ ብዙ ማስረጃዎች መገኘታቸው ገልፆ ፃፈ።

በግል ከቤተሰቡ እንደሰማሁት በወቅቱ ይዞት የነበረው ላብቶፕ ላይ ካገኙት መረጃ ውጭ ምንም ከእሱ እንዳላገኙ እና ብዙበማዕከላዊ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እና ማሰቃየት ከደረሰበት በኋላ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥም አፋጥነው ፍርድ ቤት አቅርበው ፣ 14 ዓመት ፈረዱበት፣ ፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ የጠበቃ የሚከፍለው ተቸግሮ እንደነበር ሰምቻለው።

በእስር እያለ አባቱን ተረድቶዋል፣ አንድም ቀን የትኛውም ሚዲያ ደረጄ አስታውሶ ሲፅፍ አላየሁም፣ በአነንድ ወቅት ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ መፃፉን አስታውሳለሁ ከዛ ውጭ ምንም የለም፣ በቅርቡ መንበረ በአሰባሰበችው የእስረኞች ስም ዝርዝር ውስጥ ገብቶ ሳየው ትንሽ ደስ አለኝ፣ ሆኖም ሁሌም ደረጄን ሳስብ ስንት ከቤተሰባቸው ውጭ መታሰራቸው የማይታወቅላች ስንት ኢትዮጵያዊ ይኖሩ ይሆን!?

ታስረህ ተሰቃይተህ፣ ይህን ስቃይ ከራስህ በስተቀር ማንም እንደማያቅልህ ስታውቅ ምን ይሰማህ ይሆን!? ስንቶቹ በየቀኑ የሀገር ነዋሪ፣ ዲያስፖራው፣ የውጭ መንግስታት፣ እየጮሁላቸው እንኳን እስሩ ስቃዩን መቋቋም አቅቷቸው ይቅርታ ጠይቀው፣ ወረቀት ፈርመው ከእስር እየወጡ እንደዚህ እንደደረጄ አይነቶቹ ደግሞ ማንም ሳያውቃቸው ለሁሉም መስዋአትነት ከፍለው ይኖራሉ፣ ደረጄ አሁን 6ኛ አመቱን በዝዋይ እስር እያሳለፈ እንደሆነና፣ እና በቅርቡ ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ ዞን 6 ውስጥ እንደ ሚገኝና በቅርቡ ሊፈታ እንደሚችል ቤተሰቦቹ ይናገራሉ።
ደረጄን ፍቱት!
ወንድሜን ፍቱት!
የማናውቃቸው ሁሉንም ፍቱ!
አላህ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅ!!!

LEAVE A REPLY