ኦህዴድ ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀ መንበር አድርጎ ሾመ

ኦህዴድ ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀ መንበር አድርጎ ሾመ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀ መንበር አድርጎ ሾመ። 81 አባላት ያለው የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ፤ ዶክተር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀ መንበር እንዲሁም የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ለማ መገርሳን ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር አብይ አህመድ ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የኦህዴድ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ሰርተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድርጅቱ እያሳየው ባለው የለውጥ ሂደትም ዶክተሩ ሁነኛ ሚና እዳላቸው ይነገራል።

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የ“ሀላፊነት” ሽግሽግ ያደረገበት ዋናው ምክንያት ዶክተር አብይን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እጩ አድርጎ ለማቅረብ ያለመ እንደሆነ የውስጥ አዋቂዎች እየጠቆሙ ነው።

አቶ ለማ መገርሳም የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትነታቸው እንደሚቀጥሉ ድርጅቱ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY