/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በምዕራብ ኢትዮጵያ ነቀምቴ ከተማ በተለይም ሰሞኑን የተከሰተው ህዝባዊ አመፅ ወደ ባሰ ደረጃ መሸጋገሩ ተገለጸ።
ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሀይል ስር የወደቀችው ነቀምቴ ዛሬ ማምሻውን የከተማ ከንቲባ አቶ ከበደ ሁንዴ፣ የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እራሱን “ኮማንድ ፖስት” ብሎ በሚጠራው አካል መታሰራቸው ታውቋል።
የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ ከበደ ሁንዴ ሰኞ እለት ከቄሮ ጋር ግንኙነት አለህ ተብለው በመከላከያ ሀይል ታስረው የነበረ ቢሆንም የኢሮሚያ ፖሊስ በእለቱ አስፈትቷቸው እንደነበረ ተገልጿል።በወጣቶች ላይም የጅምላ እስራትና ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ይገኛል።
በነቀምት ከተማ አለመረጋጋቱ እየተባባሰ የሄደ ሲሆን እስካሁን አንድ ሰው በጥይት ተደብድቦ ሲገደል፤ ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።በከተማ ከትናንት ጀምሮ የመብራትና የውሀ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።