‘ፓርላማ‘ው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደ

‘ፓርላማ‘ው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ መሆኑ የሚነገርለት የኢትዮጵያ  ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 9/2010ዓ.ም ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በህወሓት የሚመራው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አጸደቀው።

በምክር ቤቱ ከተገኙ 490 አባላት መካከል 395ቱ ድጋፍ ሲሰጡ 88ቱ ተቃውመዋል።7 አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት መታቀባቸው ታውቋል።

ምክር ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚጥስና ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ እየተስፋፋ በመምጣቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማጽደቅ ውሳኔ ላይ እንዳደረሰው የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የአሜሪካ መንገስትን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጆች እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያዊያን አስቸኳይ አዋጁ የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጥስ በመሆኑ “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” ውድቅ እንዲያደርገው ሲወተዉቱ መቆየታቸው ይታወቃል።

አስቸኳይ አዋጁ በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፣ በጋራ መንቀሳቀስን፣ መንግስትን የሚቃወሙ ድምፆችን ማሰማትና ምልክቶችን ማሳየት ቢከለክልም በኦሮሚያ፣ አማራና በጉራጌ ዞን አሁንም ድረስ ህዝባዊ አመፆች እየተካሄዱ ነው።

LEAVE A REPLY