አማራ አማራ ያልሆኑ መሪዎቹን ማጽዳት አለበት /ሉሉ ከበደ/

አማራ አማራ ያልሆኑ መሪዎቹን ማጽዳት አለበት /ሉሉ ከበደ/

ሀገር አቀፍ አድማ በመላ ሃገሪቱ እየተጠራ ባለበት አጋጣሚ ሁሉ በመላ ሃገሪቱ ያሉት ክልልሎች በሰመረ ሁኔታ የመደማመጥና የመናበቡ ችግር እየቀጠለ የሄደበት አጋጣሚ ያሳስባል። በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የሰመረ የተቀናጀና በፍጥነት ተግባር ላይ ሲውል የሚታየው ህዝባዊ እርምጃ የሚያኮራና አርአያነት ያለው ነው።

እርግጥ ሁሉም ባይሆኑም ክልልሎች በተለይ አማራውና ኦሮሞው ከደቡብም ጉራጌ ይህንኑ አኩሪ ተጋድሎ በተለያየ ጊዜ ይሁን እንጂ ተያይዘውታል። ሱማሌ አፋር ትግራይ ቤኔሻንጉል ጋምቤላ ደቡብ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ወያኔ ተብትቦ ያስተኛበት መተት በአማራውና በኦሮሞው ስንኝት መርከሱና ወደ አድማው መቀላቀላቸው አይቀሬ ነው።ወያኔ ሊያፈስ የተዘጋጀበትን ብዙ ደም የምናስቀረው በተባበረ አድማ የመግደያ ጉልበቱን ስናዳክም ነው።

ወያኔ በተለይም በአማራውና በኦሮሞው ክልልሎች መካከል መናበብና ባንድ ቅኝት የመጓዝ ሁኔታ እንዳይኖር አሁንም እየሰራ እንዳለ ይሰማኛል። አራቱ ድርጅቶች አሁን ያሉበትን ተክለ ቁመና እንየው። ህውሀት ከፊል የደቡብንና ሙሉ በሙሉ አፋርና የሱማሌውን ህዝብ ድርጅቶች ፍጹም ሙታን የሆኑ ግለሰቦችን በማስቀመጥ ልክ እንደ ትግራይ ክልል ለጊዜውም ቢሆን ከተቃውሞና ከአድማው ውጭ አድርጓቸዋል።

የኦፒዲኦ መሪዎች በትግላቸው በጀግንነታቸው መብታቸውን ከወያኔ መዳፍ ፈልቅቀው አውጥተዋል። ሊሆን ይገባዋል በሚሉት መንገድ የኦሮሞን ህዝብ በመምራትላይ ይገኛሉ። ከዚያም ባሻገር የብአዴን ሰዎች ቀና ብለው ወያኔን እንዲደፍሩና የአማራውን ህዝብ ከመዳፋቸው እንዲያወጡት ወኔ ሊዘሩባቸው ሞክረዋል። አንድ ግልጽ ሊሆን የሚገባው ነገር ግን የአማራው ችግር ፍጹም ውስብስብና የተለየ መሆኑን ነው።

ህውሀት ኢትዮጵያን ያለተቀናቃኝ በብቸኝነት መረከብ እንደቻለ ያኔ ባረጋገጠበት ወቅት፤ ኢሀደግ የሚል ድሪቶ ተከናንቦ መግባት እንዳለበት ስለታመነ፤ የሰበሰባቸውን ምርኮኞች ባዘጋጀው የዘር ቀንበር እየጠመደ ሲያደራጃቸው፤ ሁሉም ምርኮኞች ይሁኑ እንጂ ለጠፈጠፈው የኦሮሞ ድርጅት እንዲመሩ ያዋቀራቸው አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ሲሆኑ፤ ለደቡቡም እንደዚያው የዛው ክልል ጎሳዎች ነበሩ።

ብሄረ አማራ ብሎ ለጠፈጠፈው ድርጅት ግን አማሮችን አልነበረም እንዲመሩ የመረጠው።ምክንያቱም አማራ ከኢትዮጵያ ምድር መጥፋት የነበረበት ዘር ስለሆነ፤ አማራን የማጽዳት ስራ መስራት የሚችሉ መሆን ነበረባቸውና አማርኛን ጠንቅቀው መናገር የሚችሉ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆችና ጥቂት ደሞ ሌሎች መመረጥ ነበረባቸው። አቶ ገብረመድህን አር አያ ህውሀትን ከመሰረቱት አንጋፋ ወያኔዎች አንዱ ናቸው። አብረው በመታገል ላይ እያሉ የአማራና የኢትዮጵያ ጥላቻ እስከ አጥንታቸው የዘለቀው የህውሀት መሪዎች በግንባር ቀደምትነት ስብሀት ነጋና መለስ ዜናዊ በውቅቱ የነበረው አያያዛቸውና አስተሳሰባቸው በኢትዮጵያና በህዝቡ ላይ የሚያስከትለው አደጋ ገብረምድህንን አስፈርቷቸው አሳስቧቸው ነበር። መቀየር የሚችሉት ነገር እንደሌለ ሲረዱ፤ ድርጅቱን ጥለው ከበረሃ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ገቡ። ባንድ ወቅት ለመገናኛ ብዙሀን ባቀረቡት የምስክርነት ጽሁፋቸው ብአዴን እንዴት እንደተፈጠረ አስገራሚ ታሪክ አትመው ነበር።

በ 1972 አም አካባቢ እንደ ኢትዮጵያዘመን አቆጣጠር ኢህ አፓ በትግራይ ውስጥ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ወያኔዎቹ “ትግራይ የኛ ክልል ስለ ሆነ ውጡ ” ብለዋቸው ነበር። ኢህ አፓዎችም “ያለነው ኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ነው። ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ነው አንወጣም” ይሏቸዋል። ከዚያ በኋላ ወያኔዎቹ በድንገት ጦርነት ከፍተውባቸው እጅግ በርካታ የኢህ አፓ ተዋጊ ወጣቶችን ጨፈጨፉ። ወልቃይት ጠገዴ አካባቢ የተሰማሩ የተረፉ የኢሀፓ ሰራዊት አባላት ነበሩና ሰላሳ አምስት የሚሆኑት እጃቸውን መስጠት በመምረጣቸው ለወያኔ እጅ ሰጡ።

ኢህአፓ በዚያን ጊዜ ሰራዊቱ ከሁሉም ጎሳ የተውጣጣ ነበር።ያኔ ነው እንግዲህ በወቅቱ የነበሩት የወያኔ መሪዎች የኢሀፓን ምርኮኞች በመጠቀም አማራ የመሰሉትን ጸረ አማራ አቋም ይዘው እንዲቆሙ ማድረግ አለብን ብለው ስራ የጀመሩት። በደረሱበት ስምምነት መሰረት አማራ ጠላት እንደመሆኑ መጠን በራሳችን ትእዛዝና እንቅስቃሴ የሚታዘዝ ድርጅት መፍጠር አለብን አሉ። የአማራው ህልውና የሚጠፋበት መንገድ ከዚህ የበለጠ ስለሌለ ፕሮግራሞቹን ጽፈን ሙሉ ቁጥጥር እያደረግን እነዚህን የኢህ አፓ ወዶገቦች አደራጅተን እንጠቀምባቸው ተብሎ ውሳኔ ተላለፈ ።

ያቶ ገብረመድህን ጽሁፍ እንደሚለው።በዚህ ውሳኔ መሰረትም መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ ለሚመሰረተው የአማራ ድርጅት ፕሮግራምና የቅድመ ሁኔታ ውይይት እንዲያዘጋጁ ሃላፊነቱ ተሰጣቸው። ያዘጋጇቸውም መወያያ ርእሶች ኋላ አማራውን ለማደራጀት ፕሮግራም ሆነው የሚቀሩ ነበሩ። ህውሀት ፖሊትቢሮ ቀርበው እነ አረጋዊ በርሄና ስዩም መስፍን አንድ ላይ ሆነው የቀረበውን ጽሁፍ አንብበው ተስማሙበት። እናም እጃቸውን ከሰጡ የኢሀፓ አባላት በዋናነት ሶስት ተመርጠው ውይይቱን እንዲመሩና ምርኮኞቹን ሁሉ እንዲያሳምኑ ከዚያ ጉባኤ ተካሂዶ በወያኔ ረዳትነት ፕሮግራሙን አምነው ተቀብለው የአማራ ድርጅት እንዲመሰረት ወሰኑ። የተዘጋጀው የመወያያ ኋላም ፕሮግራም የሚሆነው ከታች ያሉትን ነጥቦች ያካተተ ነበር።

1- ነጻ አገር የነበረችው ትግራይ የራሷ መንግስትና መስተዳድር የነበራት ሀገር፤ ከአጼ ዮሃንስ ሞት በኋላ በሚኒሊክ ተወራ በአማራው ቅኝ አገዛዝ ቀንበር መውደቋን መቀበል።

2- ነጻ ሀገር የነበረችው ኤርትራ ዛሬ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ስር ወድቃ ፤ ህዝብ ለመከራና ለችግር ተዳርጓል። ከህዝባዊ ሀርነት ኤርትራ ጋር በመተባበር ኤርትራን ነጻ ማውጣት።

3- የአሁኗ ኢትዮጵያ የታሪክ ድሀና ታሪክ የሌላት ሀገር ፤ በአጼ ሚኒሊክ የተመሰረተችና ከመቶ አመታት ያነሰ ታሪክ ያላትሀገር መሆኗን አምኖ መቀበል።

4- ሚኒሊክ ግዛቱን ለማስፋፋት በመነሳት ሳይወድ በግድ “ኢትዮጵያዊነትህን ተቀበል” ተብለው በአማራው የመንግስት ስር አት በስቃይና በችግር የሚገኙ ብሄረሰቦችን “የራስን እድል በራስ መወሰን መብት እስከመገንጠል” ን፤ አምኖ መቀበል።በዚህም ላይ ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች ወህኒ ቤት መሆኗን አምኖ መቀበል።

5- አማራ የሚባል ብሄረሰብ ጨቋኝ ጸረ ህዝብ መሆኑን አምኖ መቀበል። በነዚህ መሰረታዊ የህውሀት ነጥቦች ዙሪያ ውይይት የተጀመረው እ ኢ አ ግንቦት መጨረሻ 1972 ነበር። የውይይቱ መሪዎች መለስ ዜናዊ ስብሀት ነጋና አባይ ጸሃይዬ ነበሩ። ህውሀቶች ከኢህአፓ ምርኮኞች ውስጥ ጉዳዩን አምኖ የሚቀበላቸው የአማራ ተወላጅ ለማግኘት ስድስት ወር ነው የማሳመን ስራ ለመስራት የሞከሩት። እስከ ህዳር 30/1973 ሲከራከሩ አብዛኛዎቹ የኢህ አፓ ወዶገቦች “ይህ ፕሮግራም ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ ሉአላዊነትና ጸረ ህዝብ ነው” ይሏቸው ነበር። “በህዝባችን ያልነበረና ያልታየ ፕሮግራም ተሸክመን አንታገልም። ከፈቀዳችሁ ፕሮግራሙን እራሳችን ጽፈን፤ ለአንዲት ኢትዮጵያ፤ ለአንድ ህዝብ አንድንታገል ፍቀዱ። አማራ ህዝብ ጠላት ነው የምትሉት እኛም አማራ ነን። ኩሩው አማራ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው ብላችሁ አትፈርጁ” እያሉ በእልህና በንዴት ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ኢህፓዎቹ በሶስት ተከፈሉ።

ህውሀት ጽፎ ያመጣውን አንቀበለውም ያሉ፤ ጊዜ ይሰጠንና በደንብ አንብበን ተረድተን መልስ እንስጥበት ያሉ እናም ህውሀት ያመጣው ፕሮግራም ልክ ነው ተቀብለን አማራውን ማደራጀት እንቀጥል የሚሉ ሆኑ። ከዚያ የተከተለው ነገር ጊዜ ይሰጠን ያሉት ያችን አጋጣሚ ተጠቅመው ጠፉ። አመለጡ። ግማሹ ሱዳን የቀረው ለደርግ እጅሰጠ። ፕሮግራሙን አንቀበለውም ያሉት ሁሉም አማራ ሲሆኑ አንድ የትግራይ ልጅ የገኝባቸው ነበርና ባላሰቡት ሁኔታና ሰአት እነ መለስና ስብሀት ነጋ ህውሀቶች ተሰብስበው ረሽኗቸው። በሙሉ ጨፍጭፈው ገደሏቸው። ፕሮግራሙን የተቀበሉት ዳኑ። እነማን?

“በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አምነን ተወያይተን ገምቢ ፖሊሲውን ተቀብለናል” ያሉት የሚከተሉት ሰዎች ሆኑ።

ሙሉአለም አበበ፣ አማራ

ህላዊ ዮሴፍ፣ ኤርትራ

ሃይለ ጥላሁን፣ ትግራይ፣ እድገቱ ጎጃም

ተፈራ ዋልዋ፣ ሲዳማ

ታምራት ላይኔ፣ ከንባታ

ታደሰ ካሳ፣ ትግራይ

ዮሴፍ ረታ፣ ትግራይ፣ ኤርትራ

መለሰ ጥላሁን፣ አማራ፣ ትግራይ

በረከት ስምኦን፣ ኤርትራ

ሲሳይ አሰፋ፣ ትግራይ

አዲሱ ለገሰ፣ ሂርና ሃረር

ኢያሱ በላቸው፣ ትግራይ፣ አማራ

እንግዲህ የአቶ ገብረመድህን አር አያ ጽሁፍ በሚያስረዳው መሰረት ወያኔ በነዚህ ጸረ አማራ ሰዎች ነው የአማራውን ድርጅት አቋቁሞ ለሀያሰባት አመትታት የአማራውን ህዝብ እየገደለ እያስገደለ ቁጥሩ እንዲቀንስ ያደረገው።

እነዚህ ሰዎች ዛሬም ብዙዎቹ በህይወት አሉ። ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ የተነሳው ህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ በአማራው ክልል የመንጠባጠብ ያለመናበብ አብሮ ያለመጓዝ ችግር ጎልቶ ይታይበታል። ምክንያቱ እንደ ኦሮሚያ መሪዎችጤናማና ትክክለኛ የአማራነት ስነልቡናና ወኔ ይዘው የሚወጡ አዳዲስ መሪዎች በመጥፋታቸው ነው። ኦሮሚያ ከዳር እዳር ባንዴ ሲደማመጥ አማራ መገናኛ መስመሩ ይበጣጠስበታል።

እነ በረከት ሲሞን አሉ። እነ አዲሱ ለገሰ አሉ. እነተፈራ ዋልዋ አሉ። አንድ እውነተኛ የአማራ ፋኖ ቢፈጠር ወዲያው አስር ያደርጓቸውና አንዱ አንድ ነገር ፤ ሌላው ሌላ መልክት ለህዝቡ እያስተላለፉ መደናገርን ይፈጥራሉ።ህውሀት እጅግ ፈሪ የሆኑ ሰዎች ጥርቅም ነው። ፈሪ ታግሎ ከጣለው ሰው ላይ አይነሳም። ሀያሰባት አመታት ከአማራ ላይ አልተነሳም። ወያኔ አማራን በጠላትነት ማእከል ያደረገ ትግል ሲጀምር ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ አማራ የሚባለው ህዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ተገፊ ፤ተጨቋኝ፤ ተበዳይ ፤ድሃ ፤ እንጂ ህውሃትና መሰሎቹ እንደሳሉት ጨቋኝ በዝባዥ በዳይ የስልጣን ባለቤት ሆኖ አይደለም። ግን ነው ተብሎ ከሁሉ የከፋ ሰቆቃ እየተፈጸመበት እስካሁን ዘለቀ።

ካለፉት ሀያ ሰባት አመታት በፊት የታሪክ አጋጣሚ ለነሱ አደላና ወያኔና ሻእቢያ ትልቋን ኢትዮጵያ ያለተቀናቃኝ ሲረከቡ ወያኔ አማራን እንዳሸነፈ ቆጠረ እንጂ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን ብሎ በር ከፍቶ እንዳስገባው አልተገነዘበም። ይሁንና ታዲያ አማራውን ከምድረገጽ የማጥፋት እቅዱን አጠናክሮ ቀጠለ። ሁሉንም አስገድዶ በጎሳ እንዲደራጅ ሲያደርግየሁሉም የጎሳ ድርጅት መሪዎች በህውሀት ይሁንታ ቢሆንም የሚመለመሉት የዚያው ጎሳ አባላት ናቸው። ለአማራው ግንአማርኛን መናገር የሚችሉ ትግሬዎችና ኤርትራውያን እንዲሁም የሌሎች ጎሳ አባላት ናቸው የተዋቅሩት።

በዚህም ምክንያት ተደራጅቶም ሀያሰባት አመታት በልዩ ልዩ መንገድ ዘሩ እንዲቀነስ ተደረገ። ከጅምላ ጭፍጨፋ ሴቶች እንዳይወልዱ በመርፌ እስከማምከን። አሁንም የአማራው ህዝብ ለነጻነት በተንቀሳቀሰው ሀገር አቀፍ አመጽ ውስጥ የተቀናጀና የተሟላ ሁሉን አማራ አቀፍ አመጽ እንዳያደረግ ተጽኖ ማሳደር ችለዋል። እነዚህን አማራ ያልሆኑ ጸረ አማራ የህውሀት ቅሪቶችን እርምጃ ወስዶባቸውክልሉን ካላጸዳ እነሱ እሱን ማጽዳት ይቀጥላሉ።

መላው አማራ አንድ ሆኖ በተባበረና በተቀናጀ ስልት በአመጹ እንዳይገፋ እነዚህ ነባር አመራሮች በህይወት እስካሉ ድረስ ሁሉን ያደርጋሉ። በህውሀት መሪነት አማራ እንዲዳከም እንዲንበረከክ የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። መላው አማራ ከኦሮሞውም ጋር አመጹን እንዳያቀናጅ ልዩልዩ ዘዴ በመጠቀም መሰናክል ይፈጥራሉ። ብቸኛው መፍትሄ አማራ አማራ ያልሆኑ መሪዎቹን ማጽዳት ነው።

LEAVE A REPLY