/የግል አስተያየት/
መግቢያ
ብዙ ጊዜ አዲስ ስራ ሲጀመር፣ ሀሳቡን ውይም አቅራቢውን በማኳሸሽና በማጣጣል ሃሳቡ ለቁምነገር ሳይደርስ ቶሎ ይቀጫል። ይህን በመረዳት መልካሙን ውይይት እኔም በነቀፌታ እንዳልጀምረው፣ ይህን ጽሑፍ ለማቅረብ አቅማምቸ ነበር። ዳሩ ግን፣ ከትችት ውጭ ሌላ ሀሳብን የማዳበሪያና ማሻሻያ መንገድ እንደሌለ ተገንዘቤ ይችን ጽሑፍ አዘጋጅቻለሁ። ስለዚህ፣ ውይይቱ እጅግ ጠቃሚ፣ ትችቱም አስፈላጊ ስይጣን መሆኑን መልዕክቴ በማድረግ ይዠ ቀርቤአለሁ። በፍልስፍና ወይም ጠለቅ ባለ ውይይት ላይ ሀሳብን መሰንዘር፣ ዳቦን በሳለ ቢላዎ በወግ መሸርሸር ተገቢ ነው። አለበለዚይ፣ በዶማ እጅ ዳቦውን ቆራርሶ ቅጥ ያጣ የወያኔን ገበታ (አሰተዳደር) እንዳይመስል ተስፋ አረጋለሁ።
የውይይቱ አስተናጋጆቭ ጽዮን እና ሄኖክ ውይይቱን በንቃትና ብልህነት አስተናግደዋል ብዬ አምናለሁ። ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል። አሉላ፣ ጃዋር፣ አቻምየለህና ዶ/ር ደረሰ ያቀረቡት የፖለቲካ ግንዛቤና ትምሕርት ለመረዳት ምርምርን የሚጠይቅ ሆኖ አገኝቸዋለሁ። ስለዚህ፣ ውይይቱ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አስቀድሜ እገልጻለሁ። የኢትዮጵያ ሕብረተስብ በሽግግር ያለ ስለሆነ፣ ካንድ ከቆየ ባህሪ ወደሌላ ለመሸጋገር የረጅም ጊዜ መብላላትንና መዳበርን ይጠይቃል። ሆኖም፣ አሁን በከፍተኛ ማዕበል እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያውያን ፖለቲካ፣ ሕዝቡ ይህ ነው በማይባል ጥልቅ ቋንቋ እየተወያየ እንደሆነ መግለጹ ተገቢ ነው።
ሀሳቡን የሚገልጽበት አረፍተነገር ከነ ሊቀሊቃውንት የተሻወርቅ ያወደድረዋል ብል ድፍረት አይሆንም ብየ አምናለሁ፤ እንዳይሆንም እጠይቃለሁ። ሊቁ ሆነ ብለውና ሳይሉ የሚናገሯቸውን ቃሎችና ሃሳቦች ለመረዳት ተርጓሚ ያስፈልግ ነበር ይላሉ። የአቶ ተገኝ የተሻወርቅ አባት የሆኑት፣ ሊቀሊቃውንት የተሻወርቅ የወሎና የሐረር ሰው ነበሩ። በቅኔአቸው እጅግ የታወቁ እንደነበሩ ይነገራል። የእያሱ ደጋፊ፣ የአፄ ኃይለሥላሴ ተጸናዋች እንደነበሩም ይታወቃል። የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አባት፣ አለቃ እሸቴ ጋር ጓደኛ እንደነበሩ ተወርቷል።
ሊቀሊቃውንት የተሻወርቅ ዓረፍተነገራቸው ሁሉ ጠጠር እንደነበርና በቀላሉ የማይፈታ (የማይተረጎም)ስለነበር፤ የተናገሩት ከንጉሡ ጀሮ ሲደርስ፣ ንጉሡ “አሁን ደግሞ ምን አለ?” ብለዋል ተብሏል። ማንም ሊቅ ደፍሮ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ተርጎሞ ለንጉሡ የሚነግር ሊቅ አልነበረም። ስህተት ብሆንስ! በሚል ፍራቻ። ንጉሡ ብልህም ደግም ነበሩና “በል፣ ያንተን ተወው፣ ልጅህን እናስተምረዋለን” ብለው ተገኘን ወስደው አስተምረው ለትልቅ ደረጃ አደረሱት ይባላል። ይህን ታሪክ ጎልጉየ ያለቦታው ከዚህ የጠቀስኩበት ምክንያት፣ ጽዮንና ዶ/ር ደረሰ የፌስቡክን ታዳሚ በቋንቋ አጠቃቀማቸው ዘለብ እንዲሉና ጭምትነት እንዲያሳዩ ሲማለዱ ሰምቸ ነው።
እኔ ደግሞ በፌስቡክ የሚካሄደውን የፖለቲካ ምልልስና እንካስላንቴ፣ ቋንቋችሁ ጠጥሯልና እባካችሁ አቅሉት ማለት ይሻላል ብዬ ለመጠቆም፣ የሊቀሊቃውንት ተሻወርቅን ታሪክ ምሳሌ አድርጌ አቀረብኩ። በዲሞክራሲ ገና ሳንድህ፣ ስለ መብት በአማርኛ ቋንቋ እንደሚገለጸው ከሆነ፣ አሜሪካንን ሳናስንቅ አንቀርም ባይ ነኝ። እኒህ እንግዶች የሚጠቀሙበትን አማረኛ ከሰማችሁ ትስማማላችሁ።
የወያኔ አዋጅ
በገደል አፋፍ ላይ ያለው ብረት ታጣቂው ወራሪ ወያኔ፣ ለፍጻሜው የቀረውን አስፈላጊ እርምጃ በአዋጅ አራዝሟል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ከተወያዮቹ አንዳቸውም አዋጁን አልደገፉም። አንዳዶቹ በአንዳንድ ትግሪዎች ንብረት ላይ የተፈጸመው እንዳይቀጥል የተወሰደ አስፈላጊ ርምጃ መሆኑን ለመግለጽ ሞክረዋል።
ሌሎቹ ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ ክፍለግዛቶች በሕዝብ ላይ የፈጸመው የግፍ ጭፍጨፋ ከዚህ ደረጃ እንዳደረሰው አመልክተዋል። ሕዝብ የወሰደው አጸፌታ ሳይሆን፣ የሱ በደል እንዲቆምና የሚሻውን መንግሥት እንዲያቋቁም መብቱን ለማስከበር እንደሆነ ጃዋርና አቻምየለህ ገልጸዋል። ዶ/ር ደረሰም የሕዝብን መንፈስ በምሳሌ እያረጉ አስረድተዋል። ማናቸውም የትግራይ ሰው በተራው መዘረፍና መባረር ይገባዋል አላሉም። ያሳዩት