ዶክተር መረራ ጉዲና በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በቦርድ አባልነት ተቀጠሩ

ዶክተር መረራ ጉዲና በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በቦርድ አባልነት ተቀጠሩ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዶክተር መረራ ጉዲና በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በቦርድ አባልነት መቀጠራቸውን የዩኒቨርሲቲው አስተዳድር አስታወቀ።

ዶክተር መረራ ጉዲና በህወሓት ባለስልጣናት የሚመራው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሦስት ዓመታት በፊት ካባረራቸው ወዲህ ያለ ስራ ቆይተው ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ20400 ብር(ሀያ ሺህ አራት መቶ ብር) ወርሃዊ ክፍያ በቦርድ አባልነት ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ እንደቀጠራቸው አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር በመሆን ከ25 ዓመታት በላይ ያስተማሩት ዶክተር መረራ ጉዲና ባላቸው የፖለቲካ መለካከት ብቻ በስርዓቱ ባለስልጣናት ከዩኒቨርሲቲው ከተባረሩ በሗላ ከ14 ወራት በላይ ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል።

ዶክተር መረራ በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ሊቀመንበር በመሆን እያገለገሉም ይገኛሉ።

ዩኒቨረሲቲዉ ዶክተር መረራን ለቦርድ አባልነት የመረጠበትን ምክንያት የዩኒቨርሲው ባለቤትና ማኔጂንግ ዳሬክተር የሆኑት አቶ ድንቁ ደያስ ሲገልፁ “ክቡር ዶክተር መረራ ጉዲና ከፍተኛ የስራ አመራር ክህሎት ያላቸዉ ምሁር ስለሆኑ ዩኒቨርሲቲያችንን በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ ተሹመዋል” በማለት ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY