/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ከሀላፊነት አሰናበቱ።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሬክ ቲለርሰን አምስት የአፍሪካን ሀገራት ለመጎብኘት ወደ አፍሪካ በማምራት ለሰባት ቀናት ከቆዩ በሗላ ወደ ሀገራቸው ዛሬ ማለዳ ሲመለሱ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሀላፊነታቸው እንዳነሷቸው ተገላጿል።
ሬክስ ቲለርሰን ምንም እንኳ አምስት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት መርሃ ግብር ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም ጅቡቲ፣ኢትዮጵያና ኬንያን እንደጎበኙ ፕሮግራማቸውን አሳጥረው ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደ ዋሽግተን እንዲመለሱ እንደተነገራቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቲውተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ሬክስ ቲለርሰንን ከስልጣናቸው አንስተው በምትካቸው የሲአይኤ ዳይሬክተር የነበሩትን ማይክ ፖምፔዎን ለመተካት ያበቃቸው በ“ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም”ጉዳይ ከሬክስ ቲለርሰንን ጋር ሰፊ ልዩነት በማሳየታቸው እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል።
ሬክስ ቲለርሰን አንደ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሁሉ የካበተ የፖለቲካ ልምድ እንደሌላቸው የተገለጸ ሲሆን በአሜሪካ ታሪክ 69ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ላለፉት 14 ወራት አገልግለዋል።