የዋልድባ መነኮሳት አባቶች የፍርድ ቤት ውሎ

የዋልድባ መነኮሳት አባቶች የፍርድ ቤት ውሎ

/ሀብታሙ ምናለ/

“ አባ ገ/ኢየሱስ አኹንም በደል እየደረሰባቸው ነው!” አቶ አምሃ መኮንን (ጠበቃ)

በእነ ተሸገር የከስ መዝገብ የቀረቡት 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች የዋልድባ መነኮሳት የካቲት 30 ብያኔ ለመስጠት ተቀጥረው የነበረ ሲኾን በዛሬው ችሎትም ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ለመጋቢት 10/2010ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ሰጥቷል፡፡

የመነኮሳቱ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን ለፍርድ ቤቱ፡- “አባ ገ/ኢየሱስ በማረሚያ ቤቱ ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው ነው፡፡ ከፍተኛ ጉዳትም እያጋጠማቸው አስጊ ኹኔታም ውስጥ ነው ያሉት በተጨማሪም በማስረጃነት ለፍርድ ቤት የተሰጠው ሲዲ እንዳልደረሳቸው ጠቅሰው ለኹለቱም አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጣቸው” ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪ መረጃ አቶ አምሃ የመነኮሳቱን ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጻፉት ደብዳቤ ውሳኔ አግኝቶ ለፍርድ ቤቱ የተላከ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው የመነኮሳት ችሎት ብዛት ያላቸው የሀገር ባህል ልብስ (ነጭ በነጭ) የለበሱ እናቶች ተገኝተው ችሎቱን ታድመዋል፡፡ በቁጥር ከእናቶች አነስ ቢሉም ብዛት ያላቸው ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡ እስካሁን ከነበረው ግን በጣም ብዛት ያለው ሰው ተገኝቶ ችሎቱን ታድሟል፡፡

LEAVE A REPLY