የቀድሞ ፕሬዚዳንት “የላቲን” ፊደል የኦሮምኛ ቋንቋን በእጅጉ ጎድቶታል አሉ

የቀድሞ ፕሬዚዳንት “የላቲን” ፊደል የኦሮምኛ ቋንቋን በእጅጉ ጎድቶታል አሉ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የላቲን ፊደል ለኦሮምኛ መፃፊያነት መጠቀማችን ለቋንቋው እድገት እጅግ ጎድቶታል አሉ።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ትናንት ለአማራ ክልል ር/መስተዳድር ገዱ አዳርጋቸው በጻፉት ደብዳቤ አፋን ኦሮሞ በክልሉ ማስተማር ቢጀመር የህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል ብለው እንደሚያምኑና ሁሉንም የሀገራችን ቋንቋዎችን ለመፃፉ ብቃት ያለው የራሱ የኦሮሞ ማህበረሰብም ሆነ በአፍሪካ ብቸኛ የጥቁር ህዝብ ተደርጎ የሚወሰድ የግዕዝ ፊደል እያለን “ላቲን” ለኦሮምኛ መጠቀሙ ትክክል አልነበረም ብለዋል።

መቶ አለቃ ግርማ አክለውም አፋን ኦሮሞ ተቀባይነትም ለማሳደግ ህዝብ ፍቅርና ፍላጎት እንዲኖረው ለማበረታታት የአማራ ክልል መስተዳድር ግዕዝን እንዲጠቀም በአክብሮትና በአጽንዖት እጠይቃለሁ ብለዋል።

ከዘመነ ኢህአዴግ በፊት ኦሮምኛ ቋንቋ በግዕዝ(በሳባ) ፊደል ለመጻፊያነት ለዘመናት ሲጠቀም የቆየ ሲሆን ለአብነትም መጸሐፍ ቅዱስ “መጸሐፈ ቁልቁሉ” በሚል በግዕዝ ፊደል ወደ ኦሮምኛ ተተርጉሞ በርካታ አንባቢያን ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሮምኛ ቋንቋን ለማስተማር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ባለፈው ሰኞ መግለጹ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY