የዋልድባ መነኮሳት አባቶች በፍርድቤት በድንገት በምእመናን ታጅበው ዋሉ

የዋልድባ መነኮሳት አባቶች በፍርድቤት በድንገት በምእመናን ታጅበው ዋሉ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት  የተሰየመው ችሎት በበርካታ ምእመናን ተጥለቅልቆ መዋሉ ታወቀ።

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶችና ታላላቅ ማህበራት ዘንድ ትኩረት ያልተሰጣቸው የዋልድባ መነኮሳት የፍርድ ሂደት የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በዋለው ችሎት ቁጥራቸው የበዛ የተዋህዶ ተከታዮች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የፍርድ ሂደቱ መዋሉን ምንጮች ገለጹ።

ዛሬ በዋለው ችሎት የአገዛዙ ቀኝ እጅ መሆናቸው የሚታወቀው ዳኛ ዘርኣይ አልተገኙም።

ሀብታሙ ምናለ የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ እንዲህ ገልጾታል ፡ –

በ”ህዝበ ክርስቲያን ዛሬ በአንድ ላይ በልደታ ፍርድ ቤት ተገለጠ!”

የዛሬውን የፍርድ ዉሎ በሚመለከት ጋዜጠኛና ጦምሪ
ሀብታሙ ምናለ የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ እንዲህ ገልጾታል።

ህዝበ ክርስቲያን ዛሬ በአንድ ላይ በልደታ ፍርድ ቤት ተገለጠ!”

በሽብር ክስ ተከሰው የሚገኙት የዋልድባ አባቶች የክስ ኹኔታ ለመከታተል የመጣው ህዝበ ክርስቲያን የፍርድ ቤቱን ሙሉውን መቀመጫ ምልቶት ውሏል።

በችሎቱ ላይ ሰራተኞች እስከ ስራ ቱታቸው፣ አዛውንቶች፣ እናቶችና አንስት ወጣቶች ነጠላ በማድረግ፣ ሰንበት ተማሪዎች፣ ብዛት ያላቸው ወጣቶች፣ የፍርድ ቤትሽ ሰራተኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቭስቶች በቅርብ ቀን የተፈቱ ፖለቲከኞች …. ተገኝተዋል። ቦታ በመሙላቱ ያልገቡ ሰዎችም አሉ። የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ፎቶ ያነሳሉ ብለው የገመቷቸውን ሰዎች ስልክ ቀምተዋል። ከታሰሩት መካከል ከእዚህ ቀደም የመነኮሳት ልብስ የሰጠው ወጣት ይገኝበታል። ችሎት በእንዲህ ሁኔታ ሞልቶ ሲታይ የመጀመሪያ ሲኾን በማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ዘንድም መደናገጥን ፈጥሯል።
ችሎቱ እስከ 5:10 ድረስ መጀመር አልተቻለም ነበር። ዳኞችም በሰአቱ በችሎቱ መታደም አልቻሉም።

በዛሬው ችሎት ሁለት ዳኞች ተቀይረዋል። ዘረአይም አልተሰየመም። የቀረቡት ዳኞች በማርፈዳቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።

በቀረበው አቤተታ ላይ። አቶ አምሃ ቢቀርቡም አቃቤ ህግ ግን አልሰየምም ብሏል። የሚመለከተው ማረሚያ ቤቱ ነው ብለዋል።

ፍርድ ቤቱም:- በደንብ ቁጥር 138 ላይ ሃይማኖታዊ አልባሳት ስዕሎች ደንቡ ስለሚፈቅድ ፡ማረሚያ ቤቱ ያስተካከለው እንደተጠበቀ ሆኖ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ተወስኗል። በማለት አስተላልፏል።
ከችሎት ሲወጡ ምዕመናን የመነኮሳቱን መስቀል በመሳለም ከችሎቱ ወጥተዋል።

መነኮሳቱ መጋቢት 18/2010ዓ.ም የአቃቤ ህግ ምስክርነት ሊሰማባቸው ቀጠሮ እንዳላቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY